ሀሰተኛ መታወቂያ ሰጥተዋል የተባሉ ሰራተኞች እርምጃ ተወሰደባቸው።

በህገወጥ መንገድ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ ሰጥተዋል የተባሉ 26 ሰራተኞች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገለጸ።

የሲቨል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በህገወጥ መንገድ በመንቀሳቀስ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ የሰጡ ሰራተኞች ላይ አስተማሪ የሚያደርግ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

የኤጀንሲው ዋና ዳሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት
በመገባደድ ላይ ባለው 2016 አመት ሀሰተኛ የነዋሪነት ከሰጡ ሰራተኞች ውስጥ 20 የሚሆኑት ከዚህ በፊት በተመሳሳይ መንገድ ተይዘው እርምጃ የተወሰደባቸው ነበሩ ብለዋል።

ዋና ዳሬክተሩ አክለው እንደተናገሩትም መስራቤታቸው  ለሌብነት ቦታ እንደሌለው ተናግረው ሰራተኞቹ ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል።

የሲቨል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ሌብነትና ህገወጥ አሰራሮች ለማስቀረት ዲጂታል አሰራሮችን በመተግበር ላይ እንደሚገኝ አቶ ዮናስ ተናግረዋል።

በዚህም ባሁኑ ሰአት በ104 ወረዳዎች ላይ የወረቀት መታወቂያ በማስቀረት የዲጂታል መታወቂያ እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply