ሀንጋሪ የምዕራባውያን የበላይነት አክትሟል አለች፡፡የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ምዕራባውያን በአለም አቀፍ መድረክ ለዘመናት የነበራቸው የበላይ አብቅቷል ብለዋል።የዩክሬን ጦርነ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/T75ljuXwdyX7rPj9zlxbyBm288YRMgVHwpYNR2moZwDCQ_SKZsy3hrRwuszlncxDNP9eDy8ky-GFrFLrta3gkaHAMjyY11MLP8-EWyoR6K93my7SDbwMLIWf9llbffHIViQIFhXpeMClfletRQN-bxB-CXk-nDVaXXv8Lm-O_6dW45RU3LxGVwOUvqe4amWaBYZkxSbtybR2Ya-bsc-vAq8qcfRS69SsI0noB8dgtijd-hPCiKB-KJiaDGrAZ5mrrvhnY0tDyNGaSAl1L3936Cb9moYfYbaEolHnKclA3lJGjPV55aiF1A7mSFYtptq3aqgoy3GgEfsRY5dFHrW3bw.jpg

ሀንጋሪ የምዕራባውያን የበላይነት አክትሟል አለች፡፡

የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ምዕራባውያን በአለም አቀፍ መድረክ ለዘመናት የነበራቸው የበላይ አብቅቷል ብለዋል።

የዩክሬን ጦርነት የእጅ አዙር ጦርነት ነው ያሉት ኦርባን ነገር ግን ዩክሬን ፈፅሞ ልታሸንፍ አትችልም ሲሉ ተናግረዋል።

ሀንጋሪ ምንም እንኳን የአውሮፓ ህብረትና የኔቶ አባል ሀገር ብትሆንም ማንም እንደፈለገ እንዲያዛት አትፈልግም ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሃይል አሰላለፍና ጎራ በበዛበት አለም እንደ ሀንጋሪ ያሉ ሀገራት ሉአላዊነታቸው አደጋ እየገጠመው እንደሆነም አንስተዋል።

ሀንጋሪ ለዩክሬን የሚደረገውን የጦር መሳሪያ ድጋፍ በተደጋጋሚ በመቃወሟ ከምዕራባውያን ጫና እየደረሰባት መሆኑ ይታወቃል ሲል የዘገበው አርቲ ነው።

በአባቱ መረቀ

የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply