ሀገራት በእስራኤል እና ኢራን ዉጥረት ሳቢያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ነዉ። ፈረንሳይ፣ህንድ፣ሩሲያ እና እንግሊዝ  የመሳሰሉ ሀገራት ዜጎቻቸው ወደ ኢራን እና እስራኤል እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ…

ሀገራት በእስራኤል እና ኢራን ዉጥረት ሳቢያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ነዉ።

ፈረንሳይ፣ህንድ፣ሩሲያ እና እንግሊዝ  የመሳሰሉ ሀገራት ዜጎቻቸው ወደ ኢራን እና እስራኤል እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ሀገራት ማስጠንቀቂያዎቹን የተሰጡት በሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ በሶሪያ በሚገኝ የኢራን ቆንስላ እስራኤል የወሰደችውን እርምጃ ተከትሎ ኢራን የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ማስጠንቀቋን ተከትሎ ነዉ።

ፈረንሳይ፣ህንድ፣ሩሲያ እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ ዜጎቻቸዉ ወደ እስራኤልና ፍልስጤም ግዛቶች ዜጎቻቸው እንዳይጓዙ አስጠንቅቀዋል።

ኢራን በሚያዚያ 1 በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ በእስራኤል በተፈፀመ ጥቃት ሰባት እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ አባላት እና ሁለት ጄኔራሎቾ በመገደሉ ምክንያት በእስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።

በዚህም የተነሳ በመካከለኛዉ ምስራቅ ከፍተኛ ጦርነት ይነሳል የሚል ስጋት አንዣቧል።

ዘገባዉ የአልጀዚራ ነዉ

በአቤል ደጀኔ

ሚያዝያ 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply