ሀገራችን በምግብና መጠጥ ረገድ ያላትን የቱሪዝም አቅም ያሳያል የተባለው ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በዛሬው እለት ተከፍቷል።

ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶችን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ፤ ሀገራችን በምግብና መጠጥ ረገድ ያላትን የቱሪዝም አቅም በቅርበት እንዲያውቁ ታቅዶ የተዘጋጀ ሁነት ነው ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ፌስቲቫሉ የገበያ ትስስር ለመፍጠርና ቱሪዝምን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው ተገልጧል፡፡

ይህ የምግብና መጠጥ ፌሲቲቫል ከዛሬ ሰኔ 05 ቀን/2016 ጀምሮ እስከ ሰኔ 09 ቀን 2016ዓ.ም ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይቆያል ተብሏል።

ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል የተዘጋጀው በምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል ከአሜዚንግ ፕሮሞሽንና ኢቨንት እንዲሁም ከዳብ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር መሆኑም ታውቋል፡፡

በልዑል ወልዴ

ሰኔ 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply