ሀገራዊ ውይይት እውነተኛ ትውልድን ለመፍጠርና የተደበቀን እውነታ ለማውጣት አስቻይ ይሆናል ሲሉ የብሄራዊ ውይይት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳየ ተናገሩ:: (አሻራ ሚዲያ ጷግሜ 01/13…

ሀገራዊ ውይይት እውነተኛ ትውልድን ለመፍጠርና የተደበቀን እውነታ ለማውጣት አስቻይ ይሆናል ሲሉ የብሄራዊ ውይይት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳየ ተናገሩ:: (አሻራ ሚዲያ ጷግሜ 01/13/2014 ዓ.ም) የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር የአማራ ህዝብ ብሄራዊ ጥያቄዎችን ለብሄራዊ ውይይት ኮሚሽን ለማቅረብና ችግሮችን ለይቶ ለማወቅ የተለያዩ አካላትን በማወያየት ሲሰበስብ ቆይቶል:: የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር አየለ አዲስ እንደገለጹት በአለፊት 30 አመታት የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ የአማራው ሚና ጉልህ ድርሻ እንደነበረው ጠቅሰው በሂደቱ የፖለቲካ ኢኮኖሚ አመራሮች የራሳቸውን ተግዳሮቶችና ሀላፊነቶች እንደነበሩባቸውና ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦ በአንድነት ኑሮው ለትውልድና ለልጅ ልጆቻቸው ከፍ ያለች ኢትዮጵያን ለማውረስ… እድሉ ነበራቸው ብለዋል:: ኢትዮጵያን ያለ ብሄር,ብሄር ብሄረሰቦችን ያለ ኢትዮጵያ ማሰብ አይቻልም:: በሀገራችን የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለማረም የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር የራሱን ድርሻ ለመወጣት እንዲያስችል የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ምንድን ናቸው? ኢትዮጵያን በመገንባት በኩል የአማራ ሀላፊነት ምንድን ነው? በሚል የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን,የሀገር ሽማግሌዎችን,ከሀይማኖት ተቋማት የተወከሉ አባቶችን,የፖለቲካ አመራሮችን, ሙህራንን አሰባስቦ በአምስት ዙር ምክክር ማድረጉን ዶ/ር አየለ አዲስ ገልጸዋል:: ምክክሩ በአለፉት የስርዓት ዘውግ በአማራው ህዝብ የደረሱ በደሎች ጥያቄ የሆኑ ከ107 በላይ ዋና ዋና ሀሳቦችን ማሰባሰብ ተችሏል ብለዋል:: ከነዚህ ጥያቄዎች ውስጥ በአስቸኳይ ምላሽ የሚፈልጉ,ወቅታዊ የሆኑ ስድስት አጀንዳዎችን መለየት መቻሉን ተናግረዋል:: በተነሱት ሁሉም አጀንዳዎች ላይ የሁሉም አካላት ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ የጠቀሱት ዶ/ር አየለ ለፌዴራል መንግስቱና ለብሄራዊ ውይይት ኮሚሽን በማቅረብ በሀገረ ግንባታ ስራው ላይ ሁሉም ብሄሮች በአጀንዳዎቹ ላይ ምላሽና ስራ እንዲከናወንባቸው ኮሚሽኑን እንደሚያግዙ አብራርተዋል:: የውይይት ፕሮጀክቱን ለመቅረጽ ብሄራዊ ምክክር ሂደቱ ውስጥ ተለይተው መታወቅና መታየት ያለባቸው የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ የሚለውን ለመለየትና የነጻ የውይይት ባህልን ለማደበር እንዲሁም የድርሻችንን ለመወጣት በማሰብ ፕሮጀክቱን ቀርጾ ለመንቀሳቀስ መታሰቡን የፕሮጀክቱ ዋና ሰብሳቢ ዶክተር ሰሎሞን ታቦር ገልጸዋል:: ሂደቱን ነጻ አሳታፊ እና ገለልተኛ በማድረግ የሚቻለውን ሁሉ በመፈጸም እንደተከናወነ ተናግረዋል:: በዚህም በተደረጉት መድረኮች ሁሉ የተፈለገውን የምክክር ጥያቄዎች ለመለየት መቻሉን ጠቁመዋል:: ተለይተው ከታወቁት አጀንዳዎች በመነሳት የአቋም ማሳያ መግለጫ እንደተዘጋጀ በመጠቆም የአቋም መግለጫውን ወደ ፊት ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል:: የብሄራዊ ውይይት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳየ ውይይት ከንግግር ከሽምግል እና ከሌሎችም ነገሮች ለየት የሚያደርገው ሁሉም አሸናፊ ሁነው የሚወጡበትን መንገድ ለመቀየስ መስራቱ ነው ብለዋል:: ውይይት እውነተኛ ትውልድን ለመፍጠርና የተደበቀን እውነታ ለማውጣት አስቻይ ይሆናል ብለዋል:: ኢትዮጵያ በሰላም ዘርፍ ለብዙ ሀገሮች ተምሳሌት መሆኑዋን እረስተን መከፋፈላችን አሁን ለደረስንበት መገፋፋት አንዱ መነሻ ሁኑዋል በማለት ከዚህ መጎሻሸም ለመውጣት ውይይት ማድረግ ቁልፍ ሚና መሆኑን ጠቁመዋል:: ሀገራዊ ውይይት ባለፉት ጊዜያት አለመካሄዱ አንድነትን በመሸርሸሩ ሀገራዊ ውይይት አስፈልጓል ያሉት ኮሚሽን ኮሚሽነሩ የውይይት ሂደቱ ከታች ወደ ላይ ከማህበረሰቡ ወደ አስተዳደር አካሉ እንደሚካሄድ አንስተዋል:: የመጀመሪያው ሀገራዊ ውይይት ህዳር አጋማሽ 2015 ዓ.ም አክባቢ ለማካሄድ መታቀዱንም ጠቁመዋል:: ኮሚሽን ኮሚሽነሩ የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር በአካሄደው መድረኮች የተነሱትን ጥያቄዎች እና አጀንዳዎች አስራ አንድ አባል ላለው የብሄራዊ ውይይት ኮሚቴው እንደሚያደሱ አስታውቀዋል:: በመድረኩ በውይይት ወቅት የተነሱት ጥያቄዎችንና የታሰቡትን የመፍትሄ ቁልፎችን የሚያሳይ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን ከተሳታፊዎች ተጨማሪ ጥያቄዎች ለብሄራዊ ውይይት ኮሚሽኑ ተነስተዋል:: ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply