“ሀገራዊ የምክክር መድረኩ ተቀባይነት እና ታአማኒነት ያለው እንዲሆን የሚቀርበው አጀንዳ ሀገር እና ህዝብ ያማከለ መሆን አለበት ” ተፎካካሪ ፓርቲዎች የባልደራስ ለእውነተኛ ለዲሞክራሲ ፓርቲ…

“ሀገራዊ የምክክር መድረኩ ተቀባይነት እና ታአማኒነት ያለው እንዲሆን የሚቀርበው አጀንዳ ሀገር እና ህዝብ ያማከለ መሆን አለበት ” ተፎካካሪ ፓርቲዎች

የባልደራስ ለእውነተኛ ለዲሞክራሲ ፓርቲ ‘‘በዚህ ምክክር መድረክ ላይ ብሔራዊ ጀግኖቻችን ማን ናቸው? የሚለው እና የብሔራዊ የባንዲራ ጉዳይ መነሳት” እንዳለበት ሲናገር፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) በበኩሉ‘‘ ከጥንት እስካሁን ያለው ሀገራዊ ግንባታ እንዲሁም ብሔራዊ ጀግኖች ማናቸው? በሚለው ላይ አንድ አይነት ድምዳሜ መያዝ ይገባል” ይላል፡፡

‘‘ከሁሉ በፊት በትግራይ ያለው ጦርነት ማብቃት አለበት ፤ሕውሓት እስከወዳኛው ተወግዱ ጦርነቱ ካበቃ በኃላ ሁሉንም አጀንዳዎች ወደ መድረክ አምጥቱ መነጋገሩ ይሻላል” የሚለው የትግራይ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ነው፡፡

የባልደራስ ለእውነተኛ እና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ በቃሉ አጥናፉ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቁይታ ‘‘ላለፉት ሰላሳ አመታት ወጣቱ ሲጋት ያደገው የሀሰት ትርክት አለ እዚያ ላይ በባለሙያ የታገዘ ማብራሪያ ተሰቱ ውይይት ተደርጉ በጉዳዩ ላይ መስማማት ብንችል ጥሩ ነው” ብለው፡፡

‘‘ታሪካችን ከነባራዊው ሁኔታ ወጥቶ ሌላ አድምታን ይዟል ፡፡በመሆኑን ይህንን የሀሰት ትርክት ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡ በብሔራዊ ጀግኖቻችን እና የባንዲራ ጉዳይ በደንብ መወያየት የሚፈልግ ነው” ብለዋል፡፡

በዚህ ብሔራዊ ምክክር መድረክ ምንድነው የሚያግባባን ምንስ ነው የማያግባባን የሚለውን በደንብ መለየት ያስፈልጋል የሚሉት የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ‘‘ብዙ ያተግባባንባቸው ነገሮች አሉ ሀገራዊ ግንባታው ከዚህ በፊትም እንዴት ነው አሁንስ በሚለው ላይ እና ብሔራዊ ጅግኖችን በተመለከተ በደንብ ተነጋግረን መግባባት ይገባናል” ይላሉ፡፡

አቶ ሙላቱ እንደሚሉት ባለፉት ጊዜያት የተሰሩትን ጅግንነቱችም ሆኑ ጥፋቱችን ድጋሚ እንዳይነሳ መግባባት አለብን ይላሉ፡፡

‘‘ስለዚህች ሀገር ስንል ‘ በእውነት ‘ የሸር ፤ የሲራ ፓለቲካ ሳይሆን ይህንን ሀገር በፍቅር አንድ አድርገን ለመገንባት እና ለማዝለቅ ስንል ከራስ ወዳድነት ወተን መሬት ወርደን መስራት ይገባናል” ሲሉ ያክላሉ፡፡

ለእኔ ይጠቅመኛል በሚል የሴራ ፓለቲካ ስንሰራ ኖረናል አሁን ግን ያዘመን ማብቃት አለበት ነው የሚሉት አቶ ሙላቱ ፡፡
የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሙሉ ብርሐን ሀይሌ ከኤትዩ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቁይታ እንዳሉት ‘‘ብሔራዊ መግባባት መድረኩ መካሄድ እንዳለበት እኛም ስንጠይቅ ነበር፣የትግራይ ሕዝብ የኢትዩጲያ ህዝብ አካል ነው፡፡

የትግራይ ህዝብ የኢትዩጲያ መሰረት ነው ይህ መድረክም ለዚህ ህዝብም አሰፈላጊ ነው” ካሉ በኃላ ‘‘ከሁሉ በፊት ግን ጦርነቱን በድል እንጭርስ ” ሲሉ ያብራራሉ፡፡
ይህ ብሔራዊ መግባብት ውጤታማ እንዲሆን አንዳንዱች የታሰሩ ፓለቲከኞች መፈታት አለባቸው ሲሉ አንዳንዱች ደግሞ ነገሮን በጥንቃቂ መመልከት ይገባል ነው የሚሉት፡፡

በፖለቲካ ስም ወንጀል የሰሩ እና በእነርሱ ምክንያት ብዙ ውድመት የደረሰ ሰዎችን በዚህ ሰበብ መልቅቅ በፍትህ ስርአቱ ላይ ችግር መፍጠር ነው የሚሉት የጂጂጋው ዩኒቨርስቲ የህግ መምህሩና ባለሙያው አቶ ሰለሙን ጓዴ ናቸው፡፡

ከመንግስት ጫና ራሳቸውን ለማላቀቅ እየጣሩ ያሉ ፍርድ ቤቶችን ስልጣን በዚህ ሰበብ መጋፋት አይገባም የሚሉት አቶ ሰለሙን አሁንም ቢሆን በህግ ጉዳያቸው እየተጣራ ያሉ ሰዎችን ውሳኔውን ለፍርድ ቤት መተው ይገባል ብለዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን በዛሬው እለት በአብላጫ ድምፅ አፀደቋል።

የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ በ13 ተቃውሞና አንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አዋጅ 1265/2014 ሆኖ በአብላጫ ድምፅ ነው የፀደቀው።

ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም

ያይኔ አበባ ሻምበል

Source: Link to the Post

Leave a Reply