“ሀገሬን ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እቆማለሁ!” በሚል መሪ ቃል ውይይት እየተካሄደ ነው

“ሀገሬን ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እቆማለሁ!” በሚል መሪ ቃል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)”ሀገሬን ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ውይይቱ በአዲስ አበባ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ፅህፈት ቤት ለመከላከያ ሰራዊቱ የተዘጋጀ መድረክ ሲሆን በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው፡፡

በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተገኝተዋል፡፡

እንዲሁም የከተማው ሴት አመራሮች፣ የመከላከያና የፖሊስ ከፍተኛ የሴት አመራሮች የከተማው የሴት አደረጃጀቶች መሳተፋቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

The post “ሀገሬን ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እቆማለሁ!” በሚል መሪ ቃል ውይይት እየተካሄደ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply