You are currently viewing “ሀገርን ያጸኑ አምዶችን ለማፍረስ የተያዘው እሽቅድምድም ይቁም!… የሃይማኖት ተቋማት፣ ፓርቲዎች፣ ዳያስፖራው ሀገርንና ሕዝብን የመከፋፈል ሥራ በተጠና መልኩ እየተተገበረ መሆኑን ተገንዝባች…

“ሀገርን ያጸኑ አምዶችን ለማፍረስ የተያዘው እሽቅድምድም ይቁም!… የሃይማኖት ተቋማት፣ ፓርቲዎች፣ ዳያስፖራው ሀገርንና ሕዝብን የመከፋፈል ሥራ በተጠና መልኩ እየተተገበረ መሆኑን ተገንዝባች…

“ሀገርን ያጸኑ አምዶችን ለማፍረስ የተያዘው እሽቅድምድም ይቁም!… የሃይማኖት ተቋማት፣ ፓርቲዎች፣ ዳያስፖራው ሀገርንና ሕዝብን የመከፋፈል ሥራ በተጠና መልኩ እየተተገበረ መሆኑን ተገንዝባችሁና በአንዱ ላይ የመጣው መከራ የሌላው እዳ መሆኑን ተረድታችሁ በጋራ ድምጻችሁን እንድታሰሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።” እናት፣ መኢአድ እና ኢህአፓ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ሀገርን ያጸኑ አምዶችን ለማፍረስ የተያዘው እሽቅድምድም ይቁም! በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከኢሕአፓ፣ መኢአድ እና እናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገርን ከነ ድንበሩ፣ ነጻነትን ከነ ክብሩ፣ ቋንቋን ከነ ፊደሉ፣ ኪነሕንጻን፣ ሥነጥበብን፣ ሥነሥዕልን፣ ትምህርትን፣ ሥነምግባርን፣ ታሪክን፣ አንድነትን እና ለትውልድ ጀግንነትን በማስተማር በባዕዳን ወራሪዎች ያልተደፈረች ሀገር በማስረከብ እና መሰል ታላቅ ትውፊቶችን በማስቀመጥ በኩል ከፍ ያለ ባለውለታ ነች። ይህን ውለታዋንና እሴቷን አውቀው ሊያጠፏት በሚሹ አካላት እየደረሰባት ያለው ርእዮተ ዓለማዊ ጥቃት ባለፉት 50 ዓመታት በቅርብ ጊዜያት ደግሞ ካለፉት 4 ዓመታት ወዲህ በምዕመኖቿ ላይ ጭፍጨፋ፣ በአድባራትና ገዳማቷ ላይ የሚፈጸም ተከታታይ ቃጠሎ፣ አኹን አኹን ደግሞ በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያኗንና የአምልኮ ሥርዓቷን ማቃለል፣ በአደባባይ መዝለፍና ማዋከብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ርእዮተ ዓለማዊና ታክቲካዊ ጥቃት ተው ባይ በማጣቱ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ ፖለቲካንና ማንነትን ቀይጦ የሄደ አደገኛ ጥሰት በመፈጸም ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም አፍንጫዋ ሥር በላይዋ ላይ አዲስ ሲኖዶስ ተቋቁሟል፡፡ ይህን ጉዳይ ጣልያን በወረራው ወቅት፣ በአጠቃላይ እኩይ ተልዕኮ ያላቸው የምዕራቡ ዓለም ስልት ቀያሾች ሞክረውት ያልተሳካላቸውን ቤተ ክርስቲያንን መክፈል ሀገርን መክፈል ብሎም አዲስ ክልላዊ ሀገር የማዋለድ ፕሮጀክት የማስተግበር አካል አድርገን እንመለከተዋለን፡፡ በዚህም ሂደት በተዋረድ ያሉ የመንግሥት አካላትም እጅ ሊኖርበት እንሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬ አለን፡፡ በተለይ ደግሞ መንግሥት ጥበቃውን ማንሳቱና ከተቀዳሚ ሚናው ሕግ ማስከበር ውጭ ሌላ ሚና እየያዘ መገኘቱ እጅጉን አሳስቦናል፣ አስቆጥቶናል፡፡ የአጣዬ እና አካባቢውን ጥቃት በተመለከተ፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አጣዬና አካባቢው በኢትዮጵያ ውስጥ እየፈረሰ የሚሠራ ከተማ ሆኗል፤ ሕዝብ የወደመ ከተማውን ሠርቶ ሲጨርስ እንደገና ሌላ ዙር ፍጅትና ውድመት ይቀጥላል፡፡ የአካባቢው ነዋሪ ይገደላል፣ ይሳደዳል፣ ንብረቱ ይቃጠላል፡፡ አጥፊው በውል በስሙ ሳይጠራ፣ የጉዳቱም መጠን ሳይሰላ በማግስቱ “እርቅ ወረደ” ይባላል፤ በቀናት ልዩነት አጥፊው ኃይል ራሱን የበለጠ አደራጅቶ፣ የጥፋት መጠኑን ጨምሮ አካባቢውን ያወድማል፤ ዑደቱም ይቀጥላል፤ ማስተባበያውም እንዲሁ፡፡ በዚህ ተደጋጋሚ ጥፋት ውስጥ ኩነቶችን ስናገጣጥምና ከአካባቢው ማኅበረሰብ እንደሚሰማው የመንግሥት መዋቅሩ ተሳትፎ ያደርጋል፡፡ በአጠቃላይ ግቡ እነዚሁ የጥፋት አካላት በተጋቱት ሀሰተኛ ትርክት አማራን መበቀል፣ ሕዝቡን በማራቆት ከአካባቢው ተማርሮ እንዲሰደድ ማድረግ፣ ስልታዊ ቦታዎችን በመቆጣጠር ግዛት ማስፋት፣ ብሎም አዲስ አበባን ከአፋር እና ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በመነጠል በምናብ የሳሉትን ክልላዊ ሀገር ማዋለድ ነው፡፡ በዚህ አካሄድ ነዋሪው ተደራጅቶ ራሱን እንዲከላከል ማድረግ ካልተቻለ ውጤቱ ከፍተኛ እልቂት ለመሆኑ አያጠራጥርም፡፡ የሸገር ከተማ አስተዳደርን በተመለከተ፣ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአዲስ አበባ አስተዳዳርና የኦሮሚያ ብልጽግና ዐይናችሁን ጨፍኑና ላሙኛችሁ ዓይነት አካሄድ መጀመራቸው እሙን ነው፡፡ የሸገር ከተማ ፕሮጀክትም የዚሁ አካሄድ ዋና ማሳያ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑ ሰው “አዲስ አበባን እንደ ቦሰት ወረዳ ነው የምናያት” በሌላ በኩል ደግሞ “…ጥቅም አልባ እናደርጋታለን” እንዳሉት አሻሚና ተስተካካይ ስያሜዎችን በመጠቀም አዲስ አበባን ጥቅም አልባ የማድረጉን ሴራ ወዲህም የመጠቅለሉን ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ አካል አድርገን እንወስደዋለን፡፡ ወደ አዲስ አበባ የሚያስገቡ መንግዶችን በመዝጋት እንቅስቃሴን መገደብ፣ ሥጋት መፍጠርና መክበብ (encircling)፣ ሕዝቡን ማስጨነቅ፣ አዲስ ማንነት በጉልበት መጫን፣ አካባቢዎችን እንደአዲስ መሰየም፣ የማካለል ሩጫ፣ መዝለፍ፣ ዝርፊያ፣… ዋነኞቹ የማስተግበሪያ ስልቱ አካል ሆነዋል፡፡ በተለይ የድሆችን ቤት በማፍረስ፣ ማንነትን መሠረት አድርጎ ማፈናቀል ደግሞ በአዲስ አበባ ዙሪያ በጋርመንት፣ ዓለምባንክ፣ ለሚኩራ ወረዳ 14 ቁሊቲ እና ሌሎችም አካባቢዎች በከፍተኛ መጠን እየተተገበረ ይገኛል፡፡ የሳተላይት ከተማ/ጫካ ፕሮጀክት/ በሚል ሊተገበር የታሰበው ፕሮጀክት ምን አልባት ሚሊዮኖችን ሊያፈናቅል እንደሚችል ከተጎጂዎች ጭምር አቤቱታ ደርሶናል፡፡ ልማት የሚጠላ ባይሆንም ዓለም ዛሬ ለእንስሳት ፓርክ እየከለለ መብታቸው እንዳይነካ በሕግ ጭምር በሚጠበቅበት ወቅት ይህን ያህል ሕዝብ አፈናቅሎ፣ የቤተክርስቲያንን ይዞታ ተጋፍቶ፣ በአትጠይቁኝና ማን አለብኝነት “እያለማን ነው” ማለት በጤነኛ አዕምሮ ለመታሰቡ ጥርጣሬ አለን፡፡ ይህ ነገር ባይሆን “በጎቹ ሰዎቹን በሏቸው…” ያለውን የፈላስፋ ቃል ያስታውሰናል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ የመማሪያ ቋንቋ ፖሊሲን በተመለከተ፣ የኦሮምያ ክልል አርማና መዝሙር በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ሊዘመር አይችልም በሚል የተነሣውን ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በጥድፊያና በደመነብሳዊ አካሄድ የሚተገበር የሚመስለው የአዲስ አበባ የመማሪያ ቋንቋ ፖሊሲ ዋና ግቡ በጥቂት ዓመታት ውስጥ “የእኛ ብቻ” ከሚሏት ከተማ ሌሎች ቋንቋዎችን በተለይ አማርኛን የማዳከም ተልዕኮ ነው፡፡ አለፍ ሲልም በጉልበትም ይኹን በሥነልቡናዊ ጫና የኦሮሚያ ብልጽግና “አዲስ አበባ የእኛ ብቻ ናት” የሚለውን ፕሮጀክት ማስተግበሪያ ስልት ነው፡፡ ለኢትዮጵያውያን ቋንቋ መማር መብትም ጸጋም ነው፤ ሆኖም የአንድን ድርጅት አስተሳስብ በመጫን የበላይነትን ለማስጠበቅ መሥራት አደጋው የከፋ ይሆናል፡፡ ይህን ያልተገባ አካሄድ የከተማው ነዋሪዎች ገብቷቸው ሲቃወሙ “አስጠንተናል” በሚል ሰበብ ከትምህርት ፖሊሲው እና ከሀገራዊ ምክክሩ ቀድሞ አዲስ ከተማ አቀፍ ፖሊሲ ለመተግበር መሽቀዳደም እና ይህን የብዙ ሚሊዮን ታዳጊና የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች ሕይወት በቀጥታ የሚነካ ጉዳይ ቢያንስ የከተማው ምክር ቤት እንኳን በአግባቡ ተከራክሮ ውሳኔ ሳያሳልፍበርት በአቋራጭ ለመተግበር የሚደረገው ሩጫ የከተማ አስተዳደሩን አቅጣጫ የጠፋባት መርከብ ያስመስለዋል፡፡ በአጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱት ዋና ዋና ነጥቦች ሲገጣጠሙ የኃይል የበላይነትን ማስጠበቅ፣ በተጨቁኛለሁ ትርክትና ያንን ለማካካስ “ጊዜው የእኔ ነው” በሚል ሀገርን መዝረፍ፣ መጠቅለል፣ የመምራት አቅም ማጣት፣ አለፍ ሲልም በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ አዲስ ክልል ወለድ ሀገር የመሥራት ከንቱ ምኞትን እውን ለማድረግ የታሰበ ሩጫ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ስለሆነም፡- 1. መንግሥት በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ውስጥ በተፈጠረው ችግር ተቀዳሚ ሚናው የሆነውን ሕግ የማስከበር ሥራ እንዲሠራ እንጂ በአሻማጋይነትም ሆነ በሌላ ሰበብ በተዘዋዋሪ ሕገወጥነትን ከመደገፍ በመታቀብ የቤተክርስቲያኗን ሥራ ለቤተክርስቲያኗ አመራር ብቻ እንዲተው እናሳስባለን፡፡ 2. በዚህ ሀገራችን ኹለንተናዊ ቀውስ ውስጥ በተዘፈቀችበት ወቅት የብልጽግና መንግሥት ከሞላ ጎደል ራሱን አላስፈላጊ እያደረገ፣ አለፍ ሲልም በጥፋት ውስጥ እየተሳተፈ በመሆኑ ሕዝብ ይህኑኑ ተረድቶ ራሱን ለሰላማዊ ትግል እንዲያዘጋጅ፣ አካባቢውንና ቤተዕምነቶቹን በልዩ ትኩረት እንዲጠብቅ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ 3. በአዲስ አበባ ሊተገበር የታሰበው የቋንቋ መማሪያ ፖሊሲ ከፈረሱ ጋሪው የሆነ፣ በግብታዊና ፖለቲካዊ አድሎ የተሠራ እኩይ ተግባር በመሆኑ በአፋጣኝ እንዲቆም እንጠይቃለን፡፡ 4. የሃይማኖት ተቋማት፣ ፓርቲዎች፣ ዳያስፖራው ሀገርንና ሕዝብን የመከፋፈል ሥራ በተጠና መልኩ እየተተገበረ መሆኑን ተገንዝባችሁና በአንዱ ላይ የመጣው መከራ የሌላው እዳ መሆኑን ተረድታችሁ በጋራ ድምጻችሁን እንድታሰሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! እናት ፓርቲ፣ መኢአድ እና ኢሕአፓ ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Source: Link to the Post

Leave a Reply