“ሀገር ስታምጥ” የተሰኘው የነጻነት ታጋይ አስቴር ስዩም መፅሀፍ በገበያ ላይ ዋለ፤ ከመፅሀፉ ሽያጭም 100 ሽህ ብር ተቀንሶ በመተከል እና በትግራይ ለተፈናቀሉ ወገኖች እንዲሰጥላት መልእክት…

“ሀገር ስታምጥ” የተሰኘው የነጻነት ታጋይ አስቴር ስዩም መፅሀፍ በገበያ ላይ ዋለ፤ ከመፅሀፉ ሽያጭም 100 ሽህ ብር ተቀንሶ በመተከል እና በትግራይ ለተፈናቀሉ ወገኖች እንዲሰጥላት መልእክት ከቃሊቲ ማስተላለፏም ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የነጻነት ታጋይ አስቴር ስዩም “ሀገር ስታምጥ” የተሰኘው መፅሀፍ በአድዋ ዋዜማ ምሽት ገበያ ላይ መዋሉን ባለቤቷ መ/ር በለጠ ጌትነት አስታውቋል። በብዙ መከራ የተፈተነችው አስቴር ስዩም ከመፅሀፏ ሽያጭ ከእያንዳንዱ መፅሃፍ 20 ብር ወጭ በማድረግ በድምር ከታተመው 5 ሽህ መፅሀፍ የሚገኘውን 100 ሽህ ብር ወጭ ተደርጎ በመበተከል እና በትግራይ ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን እንዲሰጥላት ከአደራ ጋር መልእክቷን ከቃሊቲ አስተላልፋለች ብሏል። ከመተከል ለተፈናቀሉ እና ከህግ ማስከበር ሂደቱ ጋር በተያያዘ ጉዳት ለደረሰባቸው የትግራይ ወገኖች እንዲሆን መወሰኗን መ/ር በለጠ ተናግሯል። አስቴር ስዩም በኢትዮጵያ ላይ የሚፈፀመውን ግፍና ጭቆና እምቢ በማለቷ ምክንያት ትላንት በመሰሪው ወያኔ ለዓመታት በእስር ቤት ተሰቃይታለች ያለው መ/ር በለጠ ዛሬም በተረኛው የኦህዴድ ቡድን ቃሊቲ እስር ቤት ከታላቁ እስክንድር ነጋ ፣ስንታየሁ ቸኮልና አስካለ ደምሌ ጋር በሀሰት ክስ እየተሰቃየች ትገኛለች ሲል አክሏል። ስለእናት ሀገሬ ኢትዮጵያ ያገባኛል በሚል መንፈስ እስር ወይም ካቴና፣ ህመሟና የልጅ ናፍቆት ሳይበግራት፤ ወጣትነቷን በእስርና በስቃይ ያሳለፈችው አስቴር ለሕዝብ ይጠቅማል ያስተምራል ያለችውን “Uገር ስታምጥ” የሚል መጽሐፍ ከእስር ቤት ሆና ለንባብ ማብቃቷን አክሎ ገልጧል። መጽሐፉን ለመግዛት የምትፈልጉ:_ ባለቤቷ መምህር በለጠ ጌትነት፣ በስልክ ቁጥር በ0918777673 እንዲሁም፣ ዘላለም አሳዬ በስልክ ቁጥር 0912400094 መደወል እንደምትችሉ ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply