ሀገር አቀፍ ውጤታማ የመምህራን የምስጋናና እውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው

ሀገር አቀፍ ውጤታማ የመምህራን የምስጋናና እውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ ውጤታማ የመምህራን የምስጋናና እውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያን ጨምሮ ሌሎች የሚኒስቴሩ የስራ ሃላፊዎች፣ መምህራን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

መርሃ ግብሩን የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ብቃት ያላቸው መምህራንንና እጩ መምህራንን ለማበረታታት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የመምህርነት ሙያ የሙያዎች ሁሉ መሰረት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ በመላ ሃገሪቱ ያሉት መምህራን ክብር እና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ሀገር አቀፍ ውጤታማ የመምህራን የምስጋና እና እውቅና መስጠት መርሃ ግብርም በየዓመቱ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ሀገር አቀፍ ውጤታማ የመምህራን የምስጋናና እውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply