ሀገር አቀፍ የሰላም ውይይት በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው

ሀገር አቀፍ የሰላም ውይይት በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመተባባር ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የሰላም ውይይት በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተውጣጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሚካሄደው ውይይት በአካባቢው እና በሀገሪቱ ፀጥታ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

ለአንድ ቀን በሚቆየው በዚሁ ውይይት የተለያዩ ሃይማኖት ተቋማት እና ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊዎች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ውይይቱን የሰላም ሚኒስቴር እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታ እና ፀጥታ ቢሮ በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ሀገር አቀፍ የሰላም ውይይት በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply