ሀገር የካደውን የህወሃት የጥፋት ቡድን የሚያወግዝ ሰልፍ በአምቦ ከተማ እየተካሄደ ነው

ሀገር የካደውን የህወሃት የጥፋት ቡድን የሚያወግዝ ሰልፍ በአምቦ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ህዳር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሃት የጥፋት ቡድን የፈፀመውን ክህደት የሚያወግዝና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ በአምቦ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የአምቦና የአካባቢዋ ነዋሪዎች እያካሄዱ ባሉት ሰልፍ አረመኔው የጥፋት ቡድን ሀገር ለማፍረስ የሚንቀሳቀስ ጠላት መሆኑን በመግለጽ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት አውግዘዋል።
መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉም አስታውቀዋል።
በከሃዲው የህወሃት ቡድን ሴራ አንድነታችን አይናጋም፣ ከጀግናው መከለከያ ሠራዊታችን ጎን እንቆማለን፣ አንድነታችንን አጠናክረን የህወሃትና የተላላኪዎቹን አፍራሽ ተልእኮን እናጋልጣለን፣ አጥፊው የህወሃት ቡድን የፈፀመውን የሀገር ክህደት እኩይ ተግባር እናወግዛለን፤ የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት ላይም መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

The post ሀገር የካደውን የህወሃት የጥፋት ቡድን የሚያወግዝ ሰልፍ በአምቦ ከተማ እየተካሄደ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply