ሁለተኛ ቀኑን በያዘዉ የዩክሬን ሰዉ አልባ አዉሮፕላን ጥቃት የሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያዎች መወደማቸዉ ተገለፀ።

ዩክሬን በትላትናው ዕለት ባደረገቹዉ ሁለተኛ የሰዉ አልባ አዉሮፕላን ጥቃት የሩሲያ የነዳጅ ዘይት ፋብሪካዎችን ከጥቅም ዉጪ አድርጋለች ተብሏል።

ከቅርብ ወራት ወዲህ በሩሲያ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በሮስኔፍት የነዳጅ ማጣሪያ ላይ የደረሰዉ ጥቃት በኢነሪጅ ዘርፉ ላይ ከደረሱ ጥቃቶች ከባዱ መሆኑ ተገልፃል።

ጥቃቱንም ተከትሎ የአቅርቦት መቆራረጥ ስጋት በመኖሩ የነዳጅ ዋጋ 2በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

የሩሲያዉ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ጥቃቱ ሀገሪቱ ለማካሄድ ቀጠሮ የያዘችዉን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማደናቀፍ የተደረገ ሙከራ ነዉ ብለዉታል።

ሩሲያ እና ዩክሬን ሁለት ዓመታትን በፈጀዉ ጦርነት ዉስጥ ለተለያዩ ወታደራዊ ዘመቻዎች ድሮን ተጠቅመዋል።

ኪዬቭ ከቅርብ ወራት ወዲህ በሩሲያ ፋብሪካዎችን እና ኢነርጂ ተቋማት ላይ ጥቃቷን አጠናክራ ቀጥላለች።

አቤል ደጀኔ
መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply