ሁለት ሻንጣ ሙሉ ብር ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸዋ በሁመራ ከተ…

ሁለት ሻንጣ ሙሉ ብር ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሁመራ ከተ…

ሁለት ሻንጣ ሙሉ ብር ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሁመራ ከተማ ሁለት ሻንጣ ሙሉ ብር ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጧል። ዋና ሳጅን ታከለ እሸቴ ይባላል ፤የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በሁመራ ከተማ ሰላም እያስከበረ ይገኛል። ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም ሰላም እያስከበረ በሚገኝበት ሁመራ ከተማ ላይ በአንድ በባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ(ባጃጅ) ላይ ሁለት ግለሰቦች ሁለት ሻንጣ ይዘው በመጓዝ ላይ ሳሉ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ ፍተሻ በሚያደርግበት ጊዜ ሁለቱም ሻንጣ ሙሉ ብር ሆኖ ተገኝቷል። በወቅቱ ግለሰቦቹ “አንዱን ሻንጣ ሙሉ ብር እንስጥህና ልቀቀን”ቢሉትም ቃል የገባለትን ህዝብ እና ሙያውን በማስበለጥ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል። በአሁኑ ሰዓት በሁለቱም ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑም ተመልክቷል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply