
#ሁለት አስቸኳይ መረጃዎች! ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ አንደኛ በቤተክህነት አከባቢ ያለው ነገር ጥሩ እንዳልሆነ ከተለያዩ ወገኖች መረጃው እየደረሰኝ ነው። የዛሬውን ስብሰባ ውጤት ለመቀልበስ ያስፈሰፈው የመንግስት ሃይል በዋናነትም የኦሮሚያ ብልጽግና ቡድን የፖሊስና ደህንነት ሃይሉን አሰማርቶ ዙሪያውን ወሮታል። አባቶች እየተዋከቡ ነው። ምዕመናን ጉዳዩን በጥንቃቄ ማየትና ለአባቶቹ እንዲደርሱላቸው ጭምር የሚገልጽ መልዕክት ነው እየተቀበልኩ ያልሁት። ዘውትር የምደውልላቸው አባትን አግኝቼ ብዙም ሳላወራቸው ስልኩን ዘጉት። ”ሌላ ጊዜ ደውል” አሉኝ። እንዲህ ብለውኝም አያውቁም። የሆነ ነገርማ አለ። ሁለተኛው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ግስጋሴ ነው። ከምንግዜውም በላይ እየቀረበ ነው። አንዳንድ ከተሞችን የተቆጣጠረ እስኪመስል ገብቶባቸዋል። ፊንጫ፡ መቂ፡ ዝዋይ ያለው ሁኔታ ጥሩ አይደለም። መንግስት ሸኔ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ሃይል ወደ መሀል እየተጠጋ ነው። መረጃው የጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ነው! “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post