ሁለገቡ የጥበብ ሰው ሳህሌ ደጋጎ

የግጥምና ዜማ ደራሲ ከመሆናቸውም ባሻገር የአጫጭር እና ረዣዥም ድራማዎች ፀሐፊ የነበሩት ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ፣ ክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ ከተጫወታቸው ሙዚቃዎች ውስጥ “ስቆ መኖር”፣ “እውነት ማሪኝ”፣ የሚሉትን ግጥሞች፣ “ዋይ ዋይ ሲሉ”፣ “ውሸት ለመናገር”፣ “ልብሽን ለአፈርሰው”፣ “ኮቱሜ”፣ የሚሉትን ዘፈኖች ግጥምና ዜማዎች የደረሱ ሲሆን ከዚህም ሌላ ለድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ “አይወጣኝም ክፉ ነገር” በሚል የዘፈነችውና በብዙሀን ዘንድ ተወዳጅነት ያለውን ሙዚቃ እንዳቀናበሩ ታሪካቸው ያሳያል፡፡

ከነዚህ የሙዚቃ ስራዎች በተጨማሪ ለብዙነሽ በቀለ ለጥላሁን ገሰሰ እንዲሁም ለሌሎች ድምጻዊያን በርካታ የሙዚቃ ግጥሞች ከመስራታቸው ባሻገር የቅንብር እና የዜማ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡ በምናብ እንግድነት በእየሩሳሌም ብርሃኑ ተጋብዘዋል ዮሃንስ አሰፋ አስተናግዷቸዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply