ሁሉም የመዝናኛ ቦታዎች ከምሽት አራት ሰአት በኃላ አገልግሎት እንዳይሰጡ ተደረገ፡፡ የወልቂጤ እና አካባቢዋ ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ከግንቦት 22/2016 ጀምሮ በተለዋጭ መግለጫ እስከሚሻር ድረ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/EzBv1bhILmK4CnjU9j6CBLFv4QnOEBwt9CLCjh1H5-XFIMeCQG2ziOsJyJ-j963yPNyaX2eLazlJLTM2LVdqS--xamhZudxC9Dw8W0p_qKu_kVfoOg01PbX5ogTCcv51P1Mry0jJY8siL_SSyu9laaha_2iLJWLm1aqsgyzXdjCIwzVTdpYDRFktHXPc0SBmMwpAUCZAYQqK7s9iFirw48wiSyQeYVZlWdxnMSYzkb57zw9TunY9pvLte3OBn_soUIAJb1jnfqJXhDlwF29zWZyIlyPVT7iFRa8qg4i5P-gH2pJirYM_vb02w5Uu8drD-TUjVr229p2-bGOKFZ3nMQ.jpg

ሁሉም የመዝናኛ ቦታዎች ከምሽት አራት ሰአት በኃላ አገልግሎት እንዳይሰጡ ተደረገ፡፡

የወልቂጤ እና አካባቢዋ ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ከግንቦት 22/2016 ጀምሮ በተለዋጭ መግለጫ እስከሚሻር ድረስ የሰዓት ገደብ እና ክልከላ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡

የሰአት ገደብ ከተጣለባቸው ጉዳች መካከል የባጃጅ ተሽከርካሪ ከምሽቱ 3:00 እስከ ንጋት 11:00 ሰአት ድረስ በከተማዋ ማንቀሳቀስ እንደማይችሉ እገዳ ተጥሎባቸዋል፡፡

እነደዚሁም ሁሉም መዝናኛ ቤቶች ማለትም ጭፈራ ቤቶች ፣ ክለቦች ግሮሰሪዎች ፣ፑልና መሰል መሰብሰቢያ ቦታዎች ከምሽቱ 4:00 በኋላ አገልግሎት መስጠት እና ያለ በቂ ምክንያት መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል፡፡

በከተማው እና በአካባቢው በየትኛውም ሰዓት በደስታም ሆነ በሃዘን፤ መሳሪያ ፣ርችት መተኮስ እና ማንኛውም አካባቢን የሚያውክ ያልተለመደ ድምጽ ማሰማት በጥብቅ እንደተከለከለ ነው ያስታወቀቀው፡፡

ከጸጥታ አስከባሪዎች እና በጸጥታ አካላት እውቅና ከሚንቀሳቀስ የጤና አንፑላንስ ውጪ የተዘረዘሩ ክልከላዎች የተላለፈ ማንኛውም ሰው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ ገልጻል።

ስለሆነም የከተማው እና የአካባቢው ነዋሪ የየአካባቢያቸው ሰላም ከመጠበቅ በተጨማሪ በጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ የተጣሉ ክልከላዎች እንዲያከብር ጥሪ አቅርቧል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply