
“ሁሉም የስቲም ተማሪዎቻችን ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡበትን ውጤት አስመዘገቡ” ባሕርዳር ዩኒቨርስቲ ስቲም ማዕከል ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስቲም ማዕከል ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አስመዘገቡ። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ 43 የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስቲም ማዕከል ተማሪዎች በሙሉ ከ375 እስከ 621 ውጤት ያመጡ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ከ50% በላይ አስመዝግበዋል። ከነዚህም ውስጥ 27ቱ ሴቶች ሲሆኑ 16ቱ ወንዶች ናቸው። አንድ ተማሪ ብቻ 375 ያስመዘገበ ሲሆን ተማሪዎች ሌሎቹ በሙሉ ከ460 በላይ ነጥብ በማምጣት ከፍተኛ ነጥብ አስመዝግበዋል። ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ስቲም ማዕከል ከባሕርዳር ከተማ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከ9-12ኛ ክፍል የሚገኙ ተማሪዎችን ከ8ኛ ወደ 9ኛ ሲዛወሩ በሂሳብ፣ በኬሚስትሪ፣ በስነህይወት፣ በፊዚክስና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከ85 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸውንና ልዩ የፈጠራ ክህሎት ያላቸው ተማሪዎችን መልምሎ መግቢያ ፈተና በመስጠት ወደዩኒቨርስቲው ስቲም ማዕከል በማስገባት በማስተማር ላይ ይገኛል። በዚህ ሂደት በዩኒቨርስቲው ትምህርታቸውን የተከታተሉና የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከወሰዱ 43 ተማሪዎች ውስጥ ሁሉም ፈተናውን ከ50% እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል። በዩኒቨርሲቲያችንም ከፍተኛው ውጤት 621 ሆኖ ተመዝግቧል። ወላጆችና፣ የዩኒቨርስቲው አመራሮች፣ መምህራንና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እንዲሁም የስቲም ማዕከል ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!!! መረጃው የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ነው። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post