ሁዋዌ በኢትዮጵያ አብረውት ከሚሰሩ አጋር ድርጅቶች ጋር የቴክኖሎጂ መረጃ ልውውጥ አደረገ

ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሁዋዌ ቴክኖሎጂ ግሩፕ፤ በኢትዮጵያ አብረውት ለሚሰሩ አጋር ድርጅቶች እና ተቋማት ጋር ኩባንያው የደረሰበት የቴክኖሎጂ ደረጃ የማስዋወቅ እና እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በሂልተን ሆቴል አከናውኗል።

ህዋዌ ቴክኖሎጂ የ2022 የኢትዮጵያ አጋርነት መርሃ ግብሩ ላይም፤ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፣ የሁዋዌ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ የኩባንያው የአገር ውስጥ አጋር ድርጅቶች እና ተቋማት ተገኝተውበታል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ እንደተናገሩት፤ ሁዋዌ በአለም ላይ ያሉ የተሻሉ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን ወደ አገራችን በማምጣት ኢትዮጵያ የወጠነችውን የኢትዮጵያ ዲጂታል ስትራቴጂ 2025 ዕውን እንዲሆን የራሱን አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።

ኩባንያው በቅርቡ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን 5ጂ ኔትወርክን እውን እንዲሆን ማድረጉን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ በርካታ መሠረተ ልማቶችን በመገንባት፣ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠርና ስማርት የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ዲጂታል ኢኮኖሚውን ለመገንባት የምናደርገውን ጥረት እየደገፈ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

“ዲጂታል ኢትዮጵያን እንገነባለን ስንል በአገር ውስጥ ተቋማት ብቻ በምንሰራው ሥራ አይደለም” ያሉት ሁሪያ ሌሎች ተቋማትም እያበረታታን በጋራ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

የህዋዊ ኢትዮጵያ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ኮዊን ስአዎ በበኩላቸው፤ ሁዋዌ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ከ158 የአገር ውስጥ አጋሮች ጋር እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው፤ ለ3ሺ 700 ዜጎችም የሥራ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል።

ሁዋዌ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ባዘጋጀው በዚህ መርሃግብር ላይም ለተለያዩ ከኩባንያው ጋር በአጋርነት የሚሰሩ ተቆማትና ድርጅቶች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply