ባንኩ ሥራ በጀመረ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተቀማጭ ገንዘቡን 5 ቢሊዮን ብር ማድረሱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
የሂጅራ ባንክ የበጀት አመቱን የሥራ አፈፃፀም አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ፣የጥቅል ትርፍ መጠኑን 162 በመቶ ማሳደጉን ገልጿል።
አመታዊ የሥራ አፈፃፃሙንና ያገኘውን ገንዘብ በመቶኛ ይፋ አድርጓል።
የደንበኞቹን ብዛትም 1 በመቶ 73 በመቶ ማሳደጉን የገለጸው ባንኩ፣
የቅርንጫፎቹ ብዛት 80 በመቶ እንደደጉም ተነስቷል።
የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም ከማል እንዳሉት የባንኩ አጠቃላይ ሀብቱ 7.1 ቢሊዮን ብር ማድረስ ተችሏል።
ሸሪዓውን መሠረት ያደረገ ከወለድ ነፃ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝና በቀጣይም ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
ከዚህ ቀደም ሂጅራ ባንክ ውጤታማ አይደለም በሚል ይነሳ የነበረውን ሃሳብ አሁን ላይ ቀይሮ ትርፋማ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋ፡፡
የባንኩ የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ሂጅራ አካታች ባንክ ነው ብለዋል።
በቀጣይም የሸሪዓን ህግ ጠብቆ ተመራጭ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ይሆናል ነው ያሉት።
ሂጅራ ባንክ ከብሄራዊ ባንክ ፍቃድ በማግኘት ሙሉ በሙሉ ሸሪዓውን መሠረት ያደረገ የወለድ አልባ አገልግሎት ለመስጠት በ2013 ዓ.ም ሥራ መጀመሩ ይታወሳል።
በአባቱ መረቀ
ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም
Source: Link to the Post