ሃላፊው የአፈር ማዳበሪያ ሲሸጥ ተያዘ፡፡በደቡብ ክልል የጎፋ ዞን የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረው ግለሰብ ለአርሶ አደርሩ እንዲከፋፈል ወደ ቀበሌው የተላከ የአፈር ማዳበሪያ ሲሸጥ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/EKTh_gzs5qEL4Rm7Qbq7_YdHXBYwLNAQfP7RxoZiXoMZoh-T5RKJLNUnaszkKamWAfSaaVGDMJ2AkEssn-VP1pF5qWI4JhP7aix7UUcddbbBFtryEl4WkhUY98kRg664zj9XdQ5xXjqa6ffBILvcesk5B_7z7YO4lunjfjhVOkMkGxbsRhVP2tUJNY2DqWSRRkADkSKOi153YOBrEWtWwUkRuuG0hpnBDVa78tUkJt-BqVOTeDuN1c7Expl1CFZSl5JAFsZj6WMSjLf4myHXKWK8RSsOgIsUNiTfIh547pg69Ve4o5oi8cS35Ixe4oFxdHmVt8BXbFRjADK8JjmRvA.jpg

ሃላፊው የአፈር ማዳበሪያ ሲሸጥ ተያዘ፡፡

በደቡብ ክልል የጎፋ ዞን የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረው ግለሰብ ለአርሶ አደርሩ እንዲከፋፈል ወደ ቀበሌው የተላከ የአፈር ማዳበሪያ ሲሸጥ ተይዟል።

የጎፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታረቀኝ ተስፋዬ እንደተናገሩት ለአርሶ አደሩ እንዲዳረስ ወደ ቀበሌው የተላከዉን 130 ኩንታል ዩርያ እና ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ በ 549ሺህ ብር በመሸጥ በሲኖትራክ ተሸከርካሪ አስጭኖ ሲሸኝ ለዞኑ ፖሊስ መምሪያ ከህዝብ በደረሰ ጥቆማ መነሻነት ሊያዝ እንደቻለ ተናግረዋል።

የቀበሌዉ የግብርና ጽህፈት ቤት ኋላፊ በሞባይል ባንኪንግ 100ሺህ ብር ተከፍሎታል ያሉት አዛዡ፣ በእጅ ከተቀበለዉ 449ሺህ ብር ጋር በመኖሪያ ቤቱ እንደተያዘ ተናግረዋል።

ማዳበሪያዉን ገዝተዋል የተባሉ አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዉለዉ ምርመራ ማጣራት መጀመሩንም የፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር ታረቀኝ ተስፋዬ ተናግረዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 06 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply