ሃገሪቱ በባለፈው 2012ዓ.ም የትምህርት ዘመን ያዘጋጀችው የበይነ-መረብ ትምህርት አሰጣጥ መመሪያ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነት ፀድቆ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡

ይሁን እንጂ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ያለው አፈፃፀም እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡በኤጀንሲው የእውቅና ፍቃድ አሰጣጥ ዳይሬክተር አቶ አብይ ደባይ ለአሀዱ እንደተናገሩት እስካሁን ድረስ 5 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቻ በበይነ-መረብ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችላቸውን መስፈርት አሟልተዋል፡፡እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ 8  የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እውቅና ለመውሰድ ኤጀንሲውን የጠየቁ ሲሆን ኤጀንሲው ያወጣውን አስቻይ መመሪያ የሚያሟሉት 5ቱ ተቋማት በቅርቡ ፍቃድ እንደሚሰጣቸው አቶ አብይ ተናግረዋል፡፡መመሪያው የሚጠይቀው መስፈርት ውስብስብና ጥንቃቄ የተሞላበት መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ በተለይም ኩረጃን ለመከላከልና ሌሎች የምዘና ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችሉ መስፈርቶች በመኖራቸው ተቋማቱ በፍጥነት ወደ ስራ እንዳይገቡ እንዳደረጋቸውም ገልፀዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply