ሃገራት ለጆ ባይደን እና ለካምላ ሃሪስ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት እያደረሱ ነው

https://gdb.voanews.com/13E88154-E767-429D-89FD-2BA021E1163A_cx0_cy2_cw0_w800_h450.jpg

የሳዑዲ አረብያ ንጉሥ ሳልማና እና ልጃቸው ልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን ተመራጩን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና ምክትላቸው ካምላ ሃሪስን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁም ተመራጩን ፕሬዚዳንት ባይደንን እና ምክትላቸው ካምላ ሃሪስን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። ኔተናያሁ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ

“ጆ ለአርባ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ የዘለቀ የሞቀ ረጅም የግል ግንኙነት ይዘን ቆይተናል። የእስራኤል ታላቅ ወዳጅ እንደሆኑም አውቃለሁ። የሃገሮቻችንን ልዩ ግንኙነት ይበልጡን ለማጠናከር፣ አብረናችሁ ልንሰራ በጉጉት እንጠብቃለን” ብለዋል።

 ጆ ባይደን ምክትላቸው ከነበሩት ከቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጋር የሻከረ ግንኙነት የነበራቸው ኔታንያሁ ኦባማን ከተኳቸው ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር በተለየ የቅርብ ግንኙነት እንደነበራቸው ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply