ሃገራት በኮሮና ቫይረስ የደበዘዘውን የፈረንጆቹን 2021 ቀድመው እየተቀበሉ ነው

ሃገራት በኮሮና ቫይረስ የደበዘዘውን የፈረንጆቹን 2021 ቀድመው እየተቀበሉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የደበዘዘውን የፈረንጆቹን አዲስ አመት አንዳንድ ሃገራት ቀድመው እየተቀበሉ ነው፡፡

በደቡብ ምዕራብ ፓሲፊክ የምትገኘው ኒውዚላንድ አዲሱን 2021 በመቀበል ቀዳሚ ሆናለች፡፡

በፓሲፊክ ደሴት የሚገኙ ሃገራት 2021ን ቀድመው የተቀበሉት ሲሆን፥ በአውስትራሊያም የጎዳና ላይ ትዕይንት በሌለበት በሲድኒ ርችት ተተኩሷል፡፡

ሌሎች ሃገራትም ባላቸው መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ አዲሱን አመት እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ይቀበሉታል፡፡

አሁን ላይ የዓለማችን ትልቁ የጤና ስጋት የሆነው ኮሮና ቫይረስ ግን አዲሱን የፈረንጆች አመት እንደወትሮው እንዳይከበር አድርጎታል፡፡

በተለይም ምዕራባውያን ዜጎቻቸው አዲሱን አመት እንደ ከዚህ ቀደሙ በአደባባይ ሳይሆን ቤታቸው ውስጥ ሆነው እንዲያከብሩ እገዳዎችን ጥለዋል፡፡

ይህን ተከትሎም በርካቶች ቤታቸው ሆነው አዲሱን አመት ይቀበሉታል ነው የተባለው፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ሃገራት በኮሮና ቫይረስ የደበዘዘውን የፈረንጆቹን 2021 ቀድመው እየተቀበሉ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply