ሄዝቦላህ፣ሃማስ እና እስላማዊ ጂሃድ ቡድን አመራሮች እስራኤልን በሚያሸንፍበት ሁኔታ ላይ መመከራቸዉ ተገለፀ።

የጋዛ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ግዜ አንስቶ በሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ ሂዞቦላህ በከእስራኤል ወታደሮች ጋር በየቀኑ የተኩስ ልዉዉጥ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልፃል።

የሊባኖሱ የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን መሪ ከሃማስ እና ከእስላማዊ ጂሃድ ከፍተኛ የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን መሪዎችን ጋር ተገናኝቶ ተወያይቷል።

በዉይይቱም በእስራኤል ላይ ሁሉን አቀፍ ድል ለማምጣት በህብረት ምን ማድረግ እንዳለባቸዉ መወያየታቸዉን የሄዝቦላህ መግጫ ያሳያል።

በትላንትናው ዕለት በነበረዉ ዉይይት ላይ የሄዝቦላዉ ሰይድ ናስራላህ፣የሃማሱ ምክትል ሀላፊ ሳላህ አል-አሩሪ እና የእስላማዊ ጂሃድ ሃላፊ ዚያድ አል-ናካላ ተገናኝተዉ የተወያዩ ሲሆን የዉይይቱን ቦታ ግን ከመግለፅ ተቋጥበዋል።

ጦርነቱ ከተጀመረ ግዜ አንስቶ ሄዝቦላህ በእስራኤል እና ሌባኖስ ድንበር ላይ ከእስራኤል ወታደሮች ጋር በየቀኑ የተኩስ ልዉዉጥ ያደርጋል።

ወር ሊሞላዉ በተቃረበዉ በዚህ ጦርነት እስካሁን ባለዉ 6500 ፍልስጤማዉያን ዜጎች መገደላቸዉን የአልጀዚራ ዘገባ ያሳያል።

በአቤል ደጀኔ

ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply