ሄዝቦላህ በእስራኤል ላይ ሮኬት ማዝነቡ ተነገረ፡፡

የሊባኖሱ ሄዝቦላህ የጦር መሪዉ በእስራኤል ጥቃት መገደሉን ተከትሎ የበቀል እርምጃ መዉሰደ መጀመሩ ተሰምቷል፡፡

ቡድኑ ከአንድ መቶ በላይ ሮኬቶችን ጋሊሌ በተሰኘችዉ ሰሜናዊ እስራኤል መተኮሱን አስታዉቋል፡፡

ጥቃቱ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በእስራኤል አይረን ዶም የአየር መቃወሚያ መክሸፋቸዉ ተነግሯል፡፡

ሄዝቦላህ ይህንን ጥቃት የፈጸመዉ የጦር አመራሩ በእስራኤል አየር ጥቃት መገደሉን ተከትሎ ነዉ፡፡

ሂዝቦላህ ታሌብ አብደላህ ወይም አቡ ታሌብ የተባለው የቡድኑ ከፍተኛ አዛዥ መገደሉን አረጋግጧል።

ከታሌብ ጋር ጁያ በተባለች መንደር ስብሰባ ላይ የነበሩ ሶስት የቡድኑ ተዋጊዎችም በአየር ጥቃቱ መገደላቸውን ሬውተርስ የደህንነት ምንጮችን ጠቅሶ አስነብቧል።

የእስራኤል ጦር አራት የሄዝቦላህ ተዋጊዎች ስለተገደሉበት ጥቃት እስካሁን ማብራሪያ አልሰጠም።

የሊባኖሱ ሄዝቦላህ የእስራኤልና ሃማስ ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ወደ እስራኤል ሚሳኤሎችን በመተኮስ ለፍልስጤማውያን አጋርነቱን አሳይቷል።

በአባቱ መረቀ

ሰኔ 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply