ህብረተሰቡ ለፓርኪንሰን ህመም ትኩረት እንዲያደርግ ተጠየቀየፓርኪንሰን ህመም እየባሰ የሚሄድና መዳን የማይችል ከባድ የአንጎል የነርቭ የጡንቻ ህመም መሆኑን ህብረተሰቡ ሊረዳ እንደሚገባ ተ…

ህብረተሰቡ ለፓርኪንሰን ህመም ትኩረት እንዲያደርግ ተጠየቀ

የፓርኪንሰን ህመም እየባሰ የሚሄድና መዳን የማይችል ከባድ የአንጎል የነርቭ የጡንቻ ህመም መሆኑን ህብረተሰቡ ሊረዳ እንደሚገባ ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ የኒዮሮሎጂክስ ህክምና ማዕከል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶከተር ሰብለ ወንጌል የፓርኪንሰን ህመም እየባሰ የሚሄድና መዳን የማችል ከባድ የአንጎል የነርቭ የጡንቻ ህመም ነው ብለዋል።

ዶክተር ሰብለ ወንጌል ይህ በሽታ ከአልዛይመር ቀጥሎ ሁለተኛው ከባድ የዓዕምሮ የነርቭ ጡንቻ ህመም ነው ሲሉ ነግረውናል ።

ዶክተር ሰብለ ወንጌል ይህን ያሉት የፓርኪንሰን ቀን በሀገራች በዛሬው ዕለት ለ13ኛ ጊዜ በፓርኪንሰን ፔሸንት ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን በጎ አድራጎት እየተከበረ በሚገኘው ኩነት ላይ ነዉ።

በአንጎል ውስጥ ያሉ አንዳንድ የነርቭ ሴሎች ወይንም ኒውሮኖች ቀስ በቀስ ሲበላሹ ወይንም ሲሞቱ የሚከሰት በሽታ ነው ተብሏአል ።

በዚህ ህመም በዋናነትኘነት የሚጠቁት ከ60ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ሲሆን በመጠኑም ቢሆን ከዛ በታች ያሉትን ሰዎች የሚያጠቃ መሆኑን ሰምተናል።

ይህ በሺታ በይበልጥ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች የሚያጠቃ ነውም ተብሏል ።

ለዚህ በሺታ መንስዔ በውል የታወቀ ነገር ባይኖርም አከባቢዎቻችን ላይ አረምን ለማጥፋት የምንጠቀማቸው የተለያዩ ኬሚካሎች፣የዘር ሀረግ ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚሆነውን ፣በየጊዜዉ በጭንቅላታችን ላይ የሚደረሱ አደጋዎች ተጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም የጉድጓድ ውሃ መጠቀም ለፓርኪንሰን በሽታ አጋላጭ መሆኑን በጥናት ተረጋግጧል ብለዋል ።

የፓርኪንሰን ህመም እንቅስቃሴን ከመገደብ በተጨማሪ ተጓኝ የጤና እክሎች የተለያዩ የአእምሮ ጤና ችግር እንደ ጭንቀት፣ቅዠት የማስታወስ ችግር ያደርሳል ተብሏል።

የፓርኪንሰን ፔሸንት ሰፖርት ዖርጋናይዜሽን በጎ አድራጎት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዘሪሁን በለው እንዳሉት ይህ ድርጂት በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ህመም ዙሪያ እርዳታ ለማድረግ የተቋቋመ ብቸኛ ተቋም ነው ብለዋል።

አቶ ዘሪሁን በአሁን ጊዜ ተቋሙ በስሩ 1200 ያህል የፓርኪንሰን ህመምተኞች እንዳሉት ጠቅሰዋል።

በመሆኑ ተቋሙ አሁን ላይ በዚህ ህመምተኞችን ለመርዳት ከአዲስ አበባ ባለፈ በኦሮሚያ ማእከላዊ ኢትዮጵያ ፣አማራ ፣ትግራይ አፋር ላይ በስፋት ለመስራት አቅደው እየሰሩ መሆኑን ነግረውናል።

አቶ ዘሪሁን ከዚህ ህመም መዳን የማይቻል ሲሆን የህመምተኞችን ህይወት ለማሻሻል የሚደረጉ እክብካቤና በሽታውን በየጊዜዉ ለመቆጣጠር የሚያግዙ መዳኒቶችን መስጠት ነው ብለዋል።

በመጨረሻም አሁን ላይ ለህመምተኞች የሚደረግ የዳይፐር፣መነፀር ፣፣ሳሙና፣እና ልዩ ልዩ የምግብና ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ የዋጋ ንረት ችግር እንደፈጠረባቸው በመግለፅ የኢትዮጲያውያን ድጋፍ ያሻናል ነዉ ያሉት፡፡

ልዑል ወልዴ

ሚያዚያ 11ቀን 2016 ዓ.ም

ኤትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጲያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply