ህብረተሰቡ ራሱንና አካባቢውን ከጥፋት ሀይሎች እንዲጠብቅ የአመራሩ ድጋፍ ያስፈልገዋል – አቶ ርስቱ ይርዳ

ህብረተሰቡ ራሱንና አካባቢውን ከጥፋት ሀይሎች እንዲጠብቅ የአመራሩ ድጋፍ ያስፈልገዋል – አቶ ርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት ራሱንና አካባቢውን ከጥፋት ሀይሎች እንዲጠብቅ የአመራሩ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተናገሩ፡፡

የደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በወቅታዊ ሃገራዊና ክልላዊ ሁኔታዎች ዙሪያና በአመራሩ ቀጣይ ተልዕኮ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም አጥፊው ቡድን አሁን በሃገር መከላከያ ላይ ግልጽ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ መንግስት ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገልፀዋል።

የጥፋት ቡድኑ ጥቃቱን የሃገሪቱን ዳር ድንበር በሚጠብቀው መከላከያ ላይ ብቻ ሳይሆን በየአካባቢው በንፁሃን ዜጎች ላይም ግጭት የመፍጠርና ጉዳት የማድረስ ሴራ ያለው በመሆኑ የክልሉ ህዝብ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን የራሱን አካባቢ በንቃት እንዲጠብቅም አሳስበዋል።

የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው ሃገርን የማፍረስ ተልዕኮ አንግቦ የቆየው የህዋሓት ጁንታ ከጥፋቱ በላይ በውሸት ፕሮፖጋንዳ ህዝቡን እንዳያደናግር ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየጊዜው እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል።

ጀግናው መከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ካለው እርምጃ በተጨማሪ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የቡድኑ ሴራና ጥፋት እንዳይኖር ህግ የማስከበር ስራ ይሰራልም ነው ያሉት፡፡

ህብረተሰቡ ከመደበኛ ስራው ሳይነቃነቅ የራሱን አካባቢ ደህንነት መጠበቅ እንዳለበት ገልጸው መንግስትና መሪው ፓርቲ የሀገሪቱንና ክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን እንዲቆም መጠየቃቸውን ከደቡብ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

The post ህብረተሰቡ ራሱንና አካባቢውን ከጥፋት ሀይሎች እንዲጠብቅ የአመራሩ ድጋፍ ያስፈልገዋል – አቶ ርስቱ ይርዳ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply