ህብረተሰቡ በዞኑ የተከሰተውን የበረሃ የአንበጣ ለመከላከል እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ አሳሰበ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥቅምት 1…

ህብረተሰቡ በዞኑ የተከሰተውን የበረሃ የአንበጣ ለመከላከል እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ አሳሰበ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 1…

ህብረተሰቡ በዞኑ የተከሰተውን የበረሃ የአንበጣ ለመከላከል እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ አሳሰበ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የግብርና መምሪያው በዞኑ የበረሃ አንበጣ ያደረሰውን ጉዳትና አሁን ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ አንበጣው በ11 ወረዳዎች በሚገኝ 55 ቀበሌዎች መከሰቱን መምሪያው ገልጿል፡፡ የመምሪያው ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት ኃይሌ እንደገለፁት፤ የአንበጣ መንጋው እስካሁን በ11 ወረዳዎችና 55 ቀበሌዎች የተከሰተ ሲሆን ከ344 ሺህ ሄ/ር የሚሆን መሬት አሰሳ ተደርጎ 71ሺ 978 ሄ/ር መሬት ላይ በሰብል፣ በቁጥቋጦ፣ በደንና በግጦሽ መሬት ላይ ተከስቷል፡፡ 29ሺህ 426 ሄ/ር የሚሆነው በደረሱ የመኸር ሰብሎች ላይ የተከሰተ ሲሆን፤ 82 በመቶ /59ሺህ 327 ሄ/ር የሚሆነውን መከላከል ተችሏል ብለዋል፡፡ የበረሃ አንበጣውን በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች 47ሺህ 633 ሄ/ር የሚሆነው በባህላዊ መንገድ መከላከል የተደረገ ሲሆን በዚህም ከ152 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍል መከላከል ስራው ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ በምንጃር ሸንኮራ፣ ቀወት፣ ሸዋሮቢት፣ኤፍራታ ግድምና በረኸት ወረዳዎች ላይ 5ሺህ 055 ሄክታር መሬት በአውሮፕላን ርጭት እንደተደረገም ገልጸዋል፡፡ በዞኑ አዋጭና ሁሉም ወረዳዎች ያሳተፈ መከላከል የተደረገው በኬሚካል የምሽት ርጭት መሆኑንና እስካሁን 11ሺህ 693 ሄ/ር የሚሆነውን መሬት በኬሚካል መከላከል መቻሉንም አንስተዋል፡፡ ኃላፊዋ አንበጣው ባደረበት አካባቢ ከ200 እሰከ 400 የሚሆን የሰው ሃይል እያደረና እየተከላከለ እንደሚገኝና ይህም መከላከል በጣርማበር ወረዳ ውጤታማ እንደነበር የገለፁ ሲሆን፤ ሌሎችም ወረዳዎች ይህንን አሰራር ሊከተሉ ይገባልም ብለዋል፡፡ በሌላ በኩልም 17ሺህ 491 ሄ/ር የሚሆነው መሬት በአንበጣው የደረሰው ጉዳት ከ0 ነጥብ 5 እስከ መቶ ፐርሰንት የደረሰ ሲሆን በስፋት ጉዳት የደረሰው በማሽላና ጤፍ ሰብሎች ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በእንስሳት መኖና በሌሎችም ሰብሎች ላይ በአንበጣ መንጋው ጉዳት የደረሰ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ብቻ በሸዋሮቢት አካባቢዎች 22 ሄ/ር መሬት ፍራፍሬ ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡ አርሶ አደሩ ከዚህ ቀደም ካለው ጋር ተዳምሮ 5ሺ 421 የኬሚካል የመርጫ መሳሪያና 6 ምርጫ የተገጠመላቸው መኪናዎች በዞኑ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡ የደረሱ ሰብሎችን ለመከላከል የዞኑ ማህበረሰብና ሌሎች የአካባቢ ተወላጆች በንቅናቄ በማሳተፍ እስካሁን 61 ሺህ ሄክታር የሚሆነውን ሰብል ማሰባሰብ የተቻለ ሲሆን ለዚህም የሚሆን 2ሺ750 ማጭድ ተሰባስቦ ለወረዳዎች መሰራጨቱን ገልጸዋል፡፡ በመከላከል ስራው ከአጎራባች ክልሎች ጋር የአንድነት ስሜት በተግባር የተረጋገጠበት ነበር ያሉት ኃላፊዋ፤ ለአብነትም የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ልዑካን ቡድን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በመገኘት በድሮን መሳሪያ ርጭት ማድረጉንም ጠቅሰዋል፡፡ የሰብል መሰብስብ ስራው በዞኑ ማህበረሰብ በመተጋገዝ እየተሰራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን የከፋ ችግር ባለባቸው 6 ወረዳዎች ስራው እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ችግሩ ለደረሰባቸው አካባቢዎች የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ ርዳታ ማቅረብ የጀመረ ሲሆን በቀወት ወረዳ ብቻ 2 ሺህ ኩንታል እህል ማድረስ መቻሉንና በሌሎችም አካባቢዎች ድጋፉ ቀጣይ ይሆናል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ለአቅመ ደጋሞች ገንዘብ በማሰባሰብና ሰብላቸውን ለማሳጨድ 46 ሺህ ብር በማሰባሰብ በምንጃርና በረኸት ወረዳዎች ተከናውኗል፡፡ በሌላ በኩልም የሰሜን ሸዋ ዞን አልማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት 21 ሺህ 500 ደብተርና 200 ኩንታል አልሚ ምግብ በዞኑ በኩል ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፤ በሌላ በአዲስ አበባ የሚገኙ የዞኑ ተወላጆች በአካልና በቁሳቁስ እገዛ እያደረጉ መሆኑን የገለፁ ሲሆን፤ ይህም ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡ ችግሩ እየከፋ መጥቷል ያሉት ወ/ሮ መሰረት በአፋር ድንበር ባሉ የዞኑ ቀበሌዎች ላይ የአንበጣ መንጋው እንደሚጨምር ሰጋቶች ያሉ ሲሆን፤ በሁሉም ወረዳዎች ህብረተሰቡ በንቅናቄ የደረሱ ሰብሎችን በጉልበትና በገንዘብ ለማንሳት ርብርብ እንዲያደርግና እስካሁን የነበረው መነሳሳት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ምንጭ፡-ሰሜን ሸዋ ዞን ኮሙኒኬሽን

Source: Link to the Post

Leave a Reply