ህብረት ባንክ የምስረታ በዓሉን 25ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ደም የመለገስ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡

ባንኩ የ25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ “የህብረት ቤተሰብ የደም ልገሳ” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሄዷል፡፡

የባንኩ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጽጌሬዳ ተስፋዬ በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙ ሲሆን፤ ባንኩ ለአስር የበጎ አድራጎት ድርጅቶችም ለእያንዳንዳቸው 1.5 ሚሊየን ብር በድምሩ 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ባንኩ ከምስረታ ጊዜ ጀምሮ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች ላይ ተሳትፎ እያደረገ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡

የባንኩ ሰራተኞች በየወሩ ከደሞዛቸው ገንዘብ በማዋጣት ለህጻናት የልብ ህሙሟ ማህበር፣ የካንሰር እና የኩላሊት ታማሚዎችን እንዲሁም ሌሎች ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸውን ስራዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ በመደገፍ ላይ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

በመሆኑም በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት፤ የባንኩን 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያ በማድረግ እንዲሁም የባንኩ መርህ በህብረት መስራት እና ማደግ በመሆኑ፤ የህብረት ቤተሰብ የደም ልገሳ በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሃ ግብር እንደተካሄደ ተነግሯል፡፡

በ1981 ዓ.ም እናታቸው ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ደም በማስፈለጉ ደም መለገስ እንደጀመሩ የተናሩት የባንኩ የአይቲ ሰርቪስ ኦፕሬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መርሻ ታደሰ በመርሃ ግብሩ ላይ የደም ልገሳ ያከናወኑ ሲሆን በ30 ዓመት ውስጥ ለ40ኛ ጊዜ ደም መለገሳቸውንም ነግረውናል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply