ህንድ ባጋጠማት የጎርፍ መጥለቅለቅ ከ25 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል፡፡ ከባድ የተባለው የጎርፍ አደጋው የመሬት መንሸራተት ያስከተለ ሲሆን የውሃው መጠን እየጨመረ እና የሃይል አቅርቦት በ…

ህንድ ባጋጠማት የጎርፍ መጥለቅለቅ ከ25 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል፡፡

ከባድ የተባለው የጎርፍ አደጋው የመሬት መንሸራተት ያስከተለ ሲሆን የውሃው መጠን እየጨመረ እና የሃይል አቅርቦት በመቋረጡም በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎችን ለከፍተኛ ችግር ዳርጓቸዋል፡፡

በህንድ ሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች ያጋጠመው ይህ አደጋ አቅራቢያ ካለው ወንዝ መሙላት በሁዋላ የተፈጠረነው ሲሉ ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል፡፡
አሳም በሚል የሚጠራው የግዛቲቱ አካባቢ የበረታው ይህ አደጋ በርካቶችን ያፈናቀለ መሆኑም ታውቋል፡፡
አደጋውን ተከትሎ ከ360 በላይ የአስቸኳይ እርዳታ ማእከላት የተቋቋሙ ሲሆን ከ95ሺህ በላይ ሰዎችን ያቀፋሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡
በአካባቢው የውሃው መጠን እየጨመረ የሚገኝ በመሆኑም በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረ ሲሆን ወደጎረቤት ባንግላዴሽም መዛመቱ ተዘግቧል፡፡

አብዱልሰላም አንሳር

ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply