ህወሀት እንደ ቺቺኒያ ያሉ ለመኖርያ ተብለው በማስተር ፕላኑ የተቀመጡ ሰፈሮችን ሙሉ በሙሉ ወደ የዘቀጠ የንግድ ሰፈርነት በመቀየር ወጣቱን ሲያደነዝዝበት የከረመ ሲሆን በአካባቢው ያሉ ቤቶችና…

ህወሀት እንደ ቺቺኒያ ያሉ ለመኖርያ ተብለው በማስተር ፕላኑ የተቀመጡ ሰፈሮችን ሙሉ በሙሉ ወደ የዘቀጠ የንግድ ሰፈርነት በመቀየር ወጣቱን ሲያደነዝዝበት የከረመ ሲሆን በአካባቢው ያሉ ቤቶችና ንግዶችን በመቆጣጠር የራሱን ሀብት ሲያጋብስ ለነዋሪው የመኖርያ ቤት እጥረት ፈጥሯል ብለዋል ኢትዮ ኤፍ ኤም ያናገራቸው በሁለቱም ማስተር ፕላኖች የተሳተፋ የአ.አ. ዩኒቨርሲቲ የከተማ ፕላን መምህር

ባለፈው ሳምንት ፤ ቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጀርባ የሚገኙት ታዋቂዎቹ በዕምነት ባርና ሬስቶራንት ቁጥር 1 እና 2 እና XOXO የምሽት ክለብ በነዋሪዎች ቅሬታ መታሸጋቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የሚነኙ ነዋሪዎቹ ጫት ማስቃሚያና የወሲብ ንግድ የሚያከናውኑ ማሳጅ ቤቶች፣ በሀሽሽ፣በመኖሪያ ቤት አካባቢ መኖር በማይፈቀድላቸው ንግድ ቤቶችን ተተንተረሰው በበረከቱ ሰርቀው አዲሱ ስታዲየም በሚደበቁ ሌቦች ተማረው ፤ ቅሬታቸውን ከወረዳ እስከ ከተማ አስተዳደሩ ድረስ ቢያቀርቡም ምንም የተቀየረ ነገር የለም ብለውናል።የምሽት ክለቦቹ ለቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች መበላሻ ሆነዋል ያሉን ነዋሪዎቹ በፓርኪጉ ምክንያት ደግሞ ለቅሶ ገጥሞን እንኳ መተላለፍ አልቻልንም ብለዋል።

የከተማ ፕላን ባለሙያው እንዳሉት ህወሀት ይሄን አካባቢ ቺቺኒያ ለማድረግ ስለፈለገች ፣ ሰዉ ተማሮ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ስታደርግ ነበር፣በዚህ ውስጥ ዲሞግራፊም ቢዝነስም አለ ይላሉ።

በአብዛኛው በአካባቢው በአሁኑ ጦርነት ህወሀትን ደግፈው የተዋጉ ጀነራሎች ከቦሌ ት/ቤት ተቆርሶ የተሰጣቸውን ቦታ አክራይተውት ነው ጭፈራ ቤቶቹ የተከፈቱት ይላሉ ነዋሪዎቹ፣ ወይም ከጀነራሎቹ በተለያየ መንገድ የተላለፈላቸው እንደ አትሌት ገብረ እግዚአብሔር ገብረማርያም ያሉ ሰዎች ናቸው ለጭፈራ ቤቶቹ ያከራይዋቸው፣ ግን ለምን? ሲሉ አከራዮቹንም ይጠይቃሉ ነዋሪዎቹ…

አትሌቱ እኔ ሳከራየው ለምግብ ቤትነት ነው ብሎናል…የአትሌቱም፣ የቦሌ ት/ቤት ዳይሬክተርም፣ እንዲሁም የየካ ክፍለ ከተማም ሀሳብ ተካቷል..ሰፋ ያለ ትንታኔውን ሔኖክ አሥራት ያቀርብልናል

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ:: ታህሳስ 26 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply