ህወሃት በንፁሀን ዜጎች ላይ እኩይ ተግባርን ለመፈፀምና ህዝቡንም ሆነ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ሆንብሎ በሃሰት ፕሮፖጋንዳ ለማደናገር ስለማቀዱ መረጃ እንደደረሰው የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። አ…

ህወሃት በንፁሀን ዜጎች ላይ እኩይ ተግባርን ለመፈፀምና ህዝቡንም ሆነ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ሆንብሎ በሃሰት ፕሮፖጋንዳ ለማደናገር ስለማቀዱ መረጃ እንደደረሰው የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። አ…

ህወሃት በንፁሀን ዜጎች ላይ እኩይ ተግባርን ለመፈፀምና ህዝቡንም ሆነ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ሆንብሎ በሃሰት ፕሮፖጋንዳ ለማደናገር ስለማቀዱ መረጃ እንደደረሰው የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 17 ቀን 3013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መንግስት በህወሃት ላይ የጀመረው ሕግን የማስከበር እርምጃ ከሁለተኛ ወደ መጨረሻውና ሦስተኛው ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን መላው የሀገራችን ሕዝቦችና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘብ ሲል የፌደራል ፖሊስ አሳስቧል። ፅንፈኛው የህወሃት ጁንታ ቡድን መቀሌ ከተማ ውስጥ በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ባልሆኑ ሰዎች ላይ አሰቃቂ ግድያ ለመፈፀም፣ ንብረታቸውን ለመዝረፍ እና ለማቃጠል መዘጋጀቱን ከነዋሪዎች የደረሰን መረጃ አመልክቷል ብሏል። ይህንን የግፍ ግድያም የመከላከያ ሠራዊትን የደንብ ልብስ በመልበስ በሰዎች ላይ ድንገት ተኩስ በመክፈት በቅርቡ በማይካድራ የፈፀመውን ብሄርን መሰረት ያደረገ አስነዋሪ፣ አሳፋሪና አሰቃቂ ጭፍጨፋ ለመድገም እቅድ አውጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው ብሏል የፌደራል ፖሊስ በመረጃው። ይህንን እኩይ ተግባር ከፈፀመም በኋላም ድርጊቱ የተፈፀመው በመንግስት ነው ብሎ በሚዲያ ለማሰራጨት የተዘጋጀ መሆኑን ከህዝብ መረጃ ደርሶናል ያለው የፌደራል ፖሊስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እና ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ይህንን የጥፋት ሴራ ተከትሎ ጁንታው ቡድን ሊያሰራጭ የተዘጋጀውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳን አስቀድሞ በመረዳትና ተቀባይነት ያጣ ዘንድ የበኩሉን እንዲወጣ ሲል አሳስቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply