“ህወሃት የአማራ ህዝብ ነቀርሳ እና በአራቱም አቅጣጫ ተተክለው ለበቀሉ እሾሆች ሁሉ ባለቤት መሆኗ ለማንም የተጋረደ አይደለም።”   ከአማራ ወጣቶች ማህበር የተላለፈ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

“ህወሃት የአማራ ህዝብ ነቀርሳ እና በአራቱም አቅጣጫ ተተክለው ለበቀሉ እሾሆች ሁሉ ባለቤት መሆኗ ለማንም የተጋረደ አይደለም።” ከአማራ ወጣቶች ማህበር የተላለፈ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

“ህወሃት የአማራ ህዝብ ነቀርሳ እና በአራቱም አቅጣጫ ተተክለው ለበቀሉ እሾሆች ሁሉ ባለቤት መሆኗ ለማንም የተጋረደ አይደለም።” ከአማራ ወጣቶች ማህበር የተላለፈ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ህወሃት የአማራ ህዝብ ነቀርሳ እና በአራቱም አቅጣጫ ተተክለው ለበቀሉ እሾሆች ሁሉ ባለቤት መሆኗ ለማንም የተጋረደ አይደለም። ለሁሉም ወሰኖቻችን መዘረፍም ሆነ ለህዝባችን መገፋት ዋነኛዋ ምክናያት ከጫካ ፍልስፍናዋ ጀምሮ በጠላትነት ፈርጃን የተነሳችዋ ይቺው ትህነግ የተባለች ግንባር ናት። ስለሆነም የህወሃትን መደምሰስ እንፈልገዋለን።እርምጃውም የማያዳግም እና አፈር ልሳ የመነሳቷን እድል የነፈገ መሆን ይኖርበታል እያልን፦ 1- በማንኛውም አጋጣሚ ይሁን በየትኛውም ጦርነት ወሰናችን እና የውስጥ ሰላማችን መደፈር ስለሌለበት ወጣቱ በንቃት አካባቢውን እና ማህበራዊ ተቋማትን እንዲጠብቅ እናሳስባለን። 2- ለህወሃት መረጃ የሚሆኑ በተቃራኒው አማራን የሚያስጠቁ እና የሚያስጠይቁ ፎቶወችን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በማህበራዊ ሚዲያ የምትለጥፉ ግለሰቦች ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ በጥብቅ እናሳውቃለን። 3- በየትኛውም አጋጣሚ አማራን ሲከፋፍል የተገኜ ወይም የታዬ ቀን እንደጣለው አውቆ፣ ከህወሃት ጋር የነበረ ማንነቱን እንደሚያሳይ ይወቅ ይረዳ፤እኛም በህወሃት ልክ ፈርጀን በሰፈረልን ልክ እንደምንከፍለው ይወቅ። 4-በሰላም ጊዜ አራሽ በጨነቀ ቀን ባለክላሽ የሆናችሁ ፋኖ ወገኖቻችን የአማራን በር ሁሉ በንቃት እንድትከታተሉ እና ለውስጥ ሰላማችን የቻላችሁን ሁሉ እንድታደርጉ እንጠይቃለን። 5-መቼም ወንድ የጨነቀ ለት ነው እና ሚፈለግ የታሰሩ የጦር መኮንንኖች እና ፋኖዎች እንዲሁም ወጣቶች እንዲፈቱ እና ለህዝባቸው እንዲደርሱ እናሳስባለን። 6- እኛ ቅሬታችንም ሆነ ጠባችን አሳዶ ከጨረሰን እና ከፀረ-ሰላሙ የትህነግ ቡድን ጋር እንጂ ከወንድማችን የትግራይ ህዝብ ጋር አለመሆኑን የትግራይ ህዝብ ይወቅልን። 7-አንደ ኢሳት ያላችሁ ሚዲያዎች ጦርነቱን የህዝብ ለማስመሰል፣ባህርዳር ላይ ያልተካሄደን ሰልፍ ተካሄደ ከሚል አይነት አላስፈላጊ ዘገባ እንድትቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply