ህወሃት የኢትዮጵያዊ አንድነት ጸር በመሆኑ መጥፋት አለበት ሲሉ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ           አሻራ ሚዲያ       ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም ባህር ዳር  አሻራ ሚዲያ ያ…

ህወሃት የኢትዮጵያዊ አንድነት ጸር በመሆኑ መጥፋት አለበት ሲሉ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም ባህር ዳር አሻራ ሚዲያ ያ…

ህወሃት የኢትዮጵያዊ አንድነት ጸር በመሆኑ መጥፋት አለበት ሲሉ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም ባህር ዳር አሻራ ሚዲያ ያነጋገራቸው የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት ለብዙ ዘመናት በመቻቻልና በአንድነት የኖረችው ኢትዮጵያ የመከፋፈልና አማራውን ያነጣጠረ ጠላትነት እንዲመነጭ ያደረገው የህወሃት ሀይል በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጥፋት ያስፈልጋል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ነዋሪነታቸውን በባህር ዳር ከተማ ያደረጉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ ግለሰቦች ለአሻራ ሚዲያ እንደገለጹት ከአሁን በኋላ ህወሃት ሳትደመሰስ መመለስ የለብንም ለመዝመትም ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ከህወሃት ተልዕኮ የተቀበሉ ግለሰቦችን ህብረተሰቡ ማጋለጥ እንደሚገባው ገልጸው ዛሬም በባህር ዳር ከተማ በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የአማራ ርስት የሆነው የወልቃይትና ራያ አካባቢዎች ወደ አማራ ክልል የሚመለሱበት ሰዓት አሁን ነው ሲሉ አስተያየት ሰጭዎች ገልጸዋል፡፡ አስተያየት ሰጭዎቹ ጦርነቱ ከእብሪተኛው ህወሃት ጋር እንጅ የአማራ እና የትግራይ ህዝቦች የሚያደርጉት ባለመሆኑ ህብረተሰቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን ከማናፈስና ከማስተጋባት መቆጠብ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ዘጋቢ ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply