You are currently viewing “ህወሓት፣ ለዓመታት ከሥልጣንም ውጭ ሆነ በሥልጣን ላይ እያለ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ጥፋትና  ውድቀት መንስኤ መሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተገነዘበው ነገር ነው፡፡” በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ…

“ህወሓት፣ ለዓመታት ከሥልጣንም ውጭ ሆነ በሥልጣን ላይ እያለ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ጥፋትና ውድቀት መንስኤ መሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተገነዘበው ነገር ነው፡፡” በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ…

“ህወሓት፣ ለዓመታት ከሥልጣንም ውጭ ሆነ በሥልጣን ላይ እያለ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ጥፋትና ውድቀት መንስኤ መሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተገነዘበው ነገር ነው፡፡” በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የቅማንት ማህበረሰብ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 29 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በወቅታዊ የኢትዮጵያ አገራችን ሁኔታ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የቅማንት ማህበረሰብ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን የተሠጠ መግለጫ:_ ራሱን የትግራይ ነፃ አውጭ (ህወሓት) ብሎ የሚጠራው ድርጅት ከተጠነሰሰበት ዕለት ጀምሮ ሽብርና ሞት፣ ጥፋትና ንብረት ማውደም እንደ ዋና አላማ ማስፈፀሚያ አድርጎ የሚንቀሳቀስ መሆኑ ለማንም ግልፅ ነው፡፡ በቀጥታ ራሱ ከሚያደርሳቸው ጥፋቶች በተጨማሪ በየቦታው ኢትዮጵያውያንን በተገኘው መንገድ በመከፋፈል እርስ በርስ አንዲጋጩ ማድረጉም እያደረገም እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ ህወሓት ባገኘው አጋጣሚ ግን የማንንም ህይወት ለመቅጠፍ የማይቸገር በመሆኑ፣ በማይካድራ ባደረገው የንፁሀን ጭፈጨፋ፣ እያወቀ፤ ብዙ የቅማንት ማህበረሰብ ተወላጆችን መግደሉ የተረጋገጠ ነው፡፡ ህወሓት ከሥልጣን ተወግዶ በትግራይ ከመሸገ ወዲህ ባደረጋቸው ወረራዎች ለማንም ህይወት የማይጨነቅ፣ ንብረት መዝረፍ ብቻ ሳይሆን የህብረተሰብ መገልገያ ተቋማትን፣ ት/ቤቶችን፣ የጤና አገልግሎት መስጫዎችን ሆን ብሎ እንዳወደመ ይታወቃል፡፡ የቤት እንስሳትን ሳይቀር የሚረሽነው ይህ ቡድን፣ አሳፋሪ የሆነ ዕድሜ ሳይለይ በቤታቸው ብቻ ሳይሆን ሴቶችን በሰዎች ፊት የደፈረ መሆኑም ይታወቃል፡፡ በተሠጠው የትግስት ጊዜ፣ ራሱን በማደራጀት፣ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች፣ በተለይም የትግራይ ህዝብ በነራስ አሉላ መሪነት ደሙን በማፍሰስ ሲዋጋቸው ከነበሩ ፀረ­ ኢትዮጵያ ሀይሎች ጋር በመወገን፣ መረጃዎች እንደሚያስገነዝቡት የትግራይን ህዝብ ህፃናትን ሣይቀር በማሰገደድና በማሰለፍ እየወረረ ነው፡፡ እኛ የመጣንበት ማህበረሰብ የሚኖርበት አካባቢ የህወሓት ጥቃት ዋናው ኢላማ ቢሆንም፣ ጥቃቱ በመላው ኢትዮጵያና በመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተሰነዘረ ነው፡፡ ህወሓት፣ ለዓመታት ከሥልጣንም ውጭ ሆነ በሥልጣን ላይ እያለ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ጥፋትና ውድቀት መንስኤ መሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተገነዘበው ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ይህ አሸባሪና ወራሪ ቡድን የሚያደርሰውን ጥቃት መመከት ብቻ ሳይሆን ለዘለቄታው እንዳይንሠራራ መመታት እንዳለበት እናምናለን፡፡ በኢትዮጵያ፣ የማህበረሰቡ ተወላጅ ወገኖቻችን በግልም ሆነ በቡድን ዘመቻውን የተቀላቀሉ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ እኛም ይህንን ወራሪ ቡድን ለመፋለም በሚደረገው እንቅስቃሴ በግንባር ከሚታገሉ ኢትዮጵያውያን ወንድሞችና እህቶቻችን ጎን በመቆም የሚቻለንን ሁሉ እናደርጋለን፡፡ በዚህ አሸባሪ ቡድን በኩል ኢትዮጵያን ለማጥቃት የሚሸርቡ ሀይሎችን ማሳፈር የሚቻለውም ይህንን ቡድን በማሰወገድ ነው፡፡ ለጋራ የሀገር ህልውና፣ ለአካባቢያችን ፀጥታና ደህንነት ለወደፊትም አብሮ ለማደግና ለመበልፀግ፣ የመጀመሪያውና ዋናው መንገድ ህወሓትና አጥፊ ተልኮውን ማስወገድ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ኢትዮጵያውያን በጋራ ሲከላከሉና ሲያጠቁ ድል የነሱ መሆኑን ታሪክ ምስክር ነው፡፡ የመጣው ጥቃትም በአካባቢ የተወሰነ ቢመስልም በመላው ኢትዮጵውያንና በሀገሪቱ ህልውና ላይ የተሰነዘረ ነው፡፡ በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ መላ ኢትዮጵያና ህዝቡን ለመታደግ ሁሉም በዚህ እንቅስቃሴ እንዲሳተፍ፣ በተለይም የቅማንት ማህበረሰብ በሚኖርበት መልክአ ምድር አቀማመጥም ምክንያት ከሌሎች ወንድሞቹ ባልተለየ መንገድ የጥቃት ሰለባ መሆኑን በመገንዘብ፣ አሁን የጀመረውን ዘመቻ በስፋት በመጨመር ድርሻውን እንዲያበረከት ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ድል ለኢትዮጵያ! ፀጋየ ታደሠ በሰሜን አሜሪካ የቅማንት ማህበረሰብ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ሰብሳቢ ነሐሴ 2014 ዓ.ም.

Source: Link to the Post

Leave a Reply