ህወሓት በሀገር መከላከያ ሰራዊት በደረሰበት ጥቃት

ህወሓት በሀገር መከላከያ ሰራዊት በደረሰበት ጥቃት አብዛኞቹ የጦር መሳሪዎች እንደወደሙበት የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ላይ ህወሓት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የከፈተው ጥቃትና እሱን ተከትሎ የተነሳው ጦርነት ሁለት ሳምንታትን አስቆጥሯል፡፡

በዚህም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ሀይል ከአስር በላይ የአየር ላይ ትቃቶችን እንደፈፀመ ተገልጿል፤ በአንፃሩ ህወሓት አራት ሮኬቶች አስወንጭፏል፡፡ሁለቱ ባህርዳርና ጎንደር ላይ ሲያርፉ ቀሪዎቹ ደግሞ በኤርትራ መዲና አስመራ መወንጨፋቸው አይዘነጋም፡፡ይህን ተከትሎ ህወሓት የተለያዩ ግዙፍ መሳሪያዎች ሊኖሩት ይችላሉ የሚል ጥርጣሬን አጭሯል፡፡ይሁንና የመከላከያ ሚኒስቴር የአንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬከተር ሜጀር ጄነራል መሃመድ ተሰማ ግንባሩ ያሉት የዘረፋቸው የጦር መሳሪያዎች እንደወደሙና ያን ያህል የሚያሰጋ ትጥቅ እንደሌለው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ህዳር 8/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply