ህወሓት እና ኦነጋውያን አንድ የሚያደርጋቸው አማራን እና አማርኛን ለማጥፋት የሚጥሩበት መንገድ ነው ሲሉ ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ተናገሩ። አሻራ ሚዲያ…

ህወሓት እና ኦነጋውያን አንድ የሚያደርጋቸው አማራን እና አማርኛን ለማጥፋት የሚጥሩበት መንገድ ነው ሲሉ ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ተናገሩ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 21 / 2013 ዓ.ም ባህር ዳር ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ከአሻራ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት ቀደም ሲል የሀገራችን መሰረታዊ ችግር የስርአት ነበር፣ በዘር ላይ የተመሰረተው የፖለቲካ ስርአት ጸረ-ዴሞክራሲ፣ ጸረ-ሰብአዊ መብትና ጸረ-ሰላም የነበረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የአንድን ቡድን የበላይነት በማንገስ የዚህን ቡድን አባላትና ደጋፊዎች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ይሰራ ነበር። በዚህም ሀገርን ዘረፈ፣ ዜጎችን የጨቋኝ ብሔር አባል ናችሁ እያለ ገደለ፣ ንብረታቸውን አወደመ፣ እንዲፈናቀሉም አደረገ። አሁንም ለውጥ አምጥቻለሁና ለውጡንም የምመራው እኔ ነኝ የሚለው ቡድን አመራር ቀደም ሲል በጎሳና በቋንቋ ላይ የተመሰረተውን ፖለቲካ አጠናክሮ በማስቀጠሉ በአንጻራዊነት ሲታይ የሁሉም ከተማ የሆነችውን አዲስ አበባን ጭምር የዚሁ የጎሳ ፖለቲካ ሰለባ እንድትሆን አደረጋት። ፊንፊኔ ኬኛ የሚለውን መዝሙር ከፍ አድርጎ በማሰማትም አማራና አማርኛን ለማዳከም ሌት ተቀን በመስራት ላይ ይገኛል። ይህንን የአንድ ቡድን የበላይነት ለማረጋገጥም በዋነኛነት በምስራቅ ወለጋና ሆሮጉድሩ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች የሚኖሩ አማሮችን ከጭፍጨፋ ለመታደግ ከመስራት ይልቅ የሞተው ሰው እናንተ የምትሉትን ያህል አይደለም በማለት የቁጥር ጫወታ ውስጥ ይገባል። ከዛም አልፎ ለምን ብለው የሚጠይቁትን እኛ ኦነግን በጽናት ብንታገልም የአማራ ብልጽግና አብንን አምርሮ ስላልታገለ ነው ችግሩ የተባባሰው በማለት ለማመካኘት ይጥራል። ይባስ ብሎ የራሷ እያረረባት የሰው ታማስላለች እንደሚባለው ኦሮሚያን በአግባቡ ማስተዳደርና በክልሉ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት ማስፈን ሳይችል በራያና ወሎ ላይ ያገባኛል ለማለት ይሞክራል። ይህም ኦነግና አጋሮቹ ቀደም ሲል ያዘጋጁት የሰሜን ኦሮሚያን ካርታ እየተረከበ መሆኑን ያመለክታል። ይህም አማራን ከፋፍሎ የኦሮሚያ ክልል ከትግራይ ጋር እንዲዋሰን ለማድረግ ታልሞ እየተሰራ መሆኑን ያመለክታል። ከዛም አልፎ የኦሮሞ ችግር በዘላቂነት ሊፈታ የሚችለው ኢትዮጵያ ስትፈርስ ነው ይል የነበረውና አሁን ላይ የጠቅላይ ሚኒስሩ የውጭ ጉዳይ አማካሪ የሆነው የቀድሞው የኦነግ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ሌንጮ ባቲ እስካሁን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነበር የታገልነው አሁን ደግሞ ኦሮሞ የበላይ የሚሆንባት ኢትዮጵያን ለመገንባት እየሰራን ነው ሲል መደመጡም የዚህ ፕሮጀክት አካል መሆኑ መታወቅ አለበት። “አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል” እንደሚባለው ይኸ ሀይል ሁሉንም ለመቆጣጠር ስለሚፈልግ መተከል ላይ ያ ሁሉ ጭፍጨፋ ሲካሄድ ሳያወግዝና ድርጊቱ እንዲቆምም ሳያሳስብ ዝም ብሎ የቆየ ፖለቲከኛ ነኝ ባይ ሁሉ ትህነግ ሙሉ በሙሉ ሲወገድና በመሰረቱ እንቅፋት መሆኑ ሲያበቃ ሁሉም ነገር ወደሱ እንደሚዞር ስለሚያውቅ የርስት ፖለቲካ በማንሳት አማራ ላይ ጣቱን ለመቀሰር ይውተረተራል። እናም ከዚህ አዙሪት ወጥተን ሀገራችን በትክክለኛው የለውጥ ጎደና ላይ እንድትራመድና የህዝቦቿን አንድነትና እኩል ተጠቃሚነት አጠናክራ እንድትጓዝ ከተፈለገ ከተረኝነት ፖለቲካና ስግግብ ፍላጎት ራስን አርቆ ሀገር እንደሚመራ አካል ማሰብን ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል። በዚህ ልክ ማሰብና መተግበር ካልቻልን ሁሉን ለመጨበጥ ፈልገን አንዱንም ሳንይዝ እንዳንቀር መጠንቀቅ ይኖርብናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply