ህወሓት እና ኦነግ ሸኔ በአሸባሪነት ሊፈረጁ ይገባል ሲል ባልደራስ ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲ…

ህወሓት እና ኦነግ ሸኔ በአሸባሪነት ሊፈረጁ ይገባል ሲል ባልደራስ ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በዛሬው ዕለት ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በዋና ፅ/ቤቱ ለሚዲያዎች በሰጠው መግለጫ ህወሓትና ኦነግ በአሸባሪነት ሊፈረጁ ይገባል ሲል ጠይቋል። በመግለጫው በዋናነት ከተነሱት አበይት ጉዳዮች መካከል ህወሓትና ኦነግ ሸኔ የተባሉ ፀረ ኢትዮጵያ የሆኑ ድርጅቶች ፖለቲካን ሽፋን አድርገው በዘረፉት ገንዘብ የተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶች ተወርሰው ለአገርና ለህዝብ ጥቅም እንዲውሉ የሚጠይቀው ይገኝበታል። በተጨማሪም አሁን ያለው ሕገ መንግስት የህወሓትና የኦነግ የበኩር ልጅ በመሆኑ በአስቸኳይ ከምርጫ በፊት ታግዶ ህዝቡ ተወያይቶ አዲስ የመተዳደሪያ ሰነድ እንዲመሰረትም ጠይቋል። በህወሓት በኅይል የተነጠቁ ከሰሜን ጎንደር ( ወልቃይት ጠገዴ ጠለምትና ሁመራ ) እንዲሁም ከሰሜን ወሎ በኃይል የተነጠቀው ራያ ወደ ቀድሞ ይዞታው አማራ ክልል እንዲካተት መደረጉ አግባብና ፍትሃዊ እንደሆነ ያምናል ብሏል። የአማራ ብልፅግና የያዘው ወቅታዊ አቋም በተለይም በሕገመንግስት መሻሻል እና ከሽብርተኛው ህወሓት በአማራ ልዩ ሃይል ሚሊሻና መከላከያ ሰራዊቱ አማካኝነት በተመለሱ የቀድሞ ዕርስቶቹ (ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ጠለምት ሁመራ እና ራያ) ዙሪያ የሚደነቅ ነው፤ ይቀጥልበትም ብሏል። በስተመጨረሻም የህሊና(የፖለቲካ) እስረኞች የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች እነ እስክንድር ነጋ እንዲሁም የኢዴፓ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው በአስቸኳይ እንዲፈቱ ባልደራስ ስለመጠየቁ ከፓርቲው ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው የተገኘ መረጃ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply