ህወሓት ከማረሚያ ቤት በመልቀቅ ለዘረፋ ያሰማራቸውን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን የፌደራል ፖሊስ ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 12 ቀን 2013…

ህወሓት ከማረሚያ ቤት በመልቀቅ ለዘረፋ ያሰማራቸውን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን የፌደራል ፖሊስ ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 12 ቀን 2013…

ህወሓት ከማረሚያ ቤት በመልቀቅ ለዘረፋ ያሰማራቸውን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን የፌደራል ፖሊስ ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ ዛሬ በመቀሌ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። ምክትል ኮሚሽነር በዚህን ወቅት ጁንታው ከተሞችን ለቆ ከመሸሹ በፊት በማረሚያ ቤት የነበሩ ወንጀለኞችን መሳሪያ አስታጥቆ በመልቀቅ በከተሞች አካባቢ ዝርፊያ እንዲፈጽሙ ማድረጉን ገልፀዋል። እነዚህ ወንጀሎች የመንግስት ተቋማትን ንብረት ጭምር መዝረፋቸውን መናገራቸውን የኢዜአ ዘገባ አመልክቷል። የፌደራል ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ስር የማዋሉን ስራ አጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቀዋል። ወንጀለኞቹ የታጠቁትን የጦር መሳሪያዎች የማስፈታቱ ተግባር እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል። በተጨማሪም ህገ-ወጡ የህወሃት ጁንታ በመንግስት ተቋማት ያሉ ሰነዶችንና ሰነድ የያዙ ኮምፒውተሮችን አቃጥሎ መሸሸኑም ገልጸዋል። ይህም ቡድኑ ከራሱ ስልጣን ውጭ ለህዝብ ምንም አይነት ዴንታ የሌለው መሆኑን ያመላክታል ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply