ህወሓት ከነ አስተምህሮው ከኢትዮጵያ ምድር መጥፋት አለበት! ከሐረር ፍትህና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ [ሐፍዴፓ] የተሰጠ መግለጫ ህዳር ፳፩ ቀን ፳፻፳ በቅድሚያ ከግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ጀ…

ህወሓት ከነ አስተምህሮው ከኢትዮጵያ ምድር መጥፋት አለበት! ከሐረር ፍትህና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ [ሐፍዴፓ] የተሰጠ መግለጫ ህዳር ፳፩ ቀን ፳፻፳ በቅድሚያ ከግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ጀ…

ህወሓት ከነ አስተምህሮው ከኢትዮጵያ ምድር መጥፋት አለበት! ከሐረር ፍትህና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ [ሐፍዴፓ] የተሰጠ መግለጫ ህዳር ፳፩ ቀን ፳፻፳ በቅድሚያ ከግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ጀሞሮ እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ላይ ታሪክ ይቅር የማይለዉ ክህደት ሲፈፅም የኖረው ህወሓት የተሰኘን የጠባብ ጎሰኞች ቡድን የሚገባዉን ዉርደት ባስተማማኝ ሁኔታ እና ፍጥነት ላከናነቡት እና ለታላቋ ኢትዮጵያ ትንሣኤ ጎህ ለቀደዱልን ዉድ ኢትዮጵያውያን መለዮ ለባሾች ያለንን ክብር እና ምስጋና ለመግለፅ እንወዳለን!! ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ክልል ልዩ ኃይል፣ እና ለአማራ ክልል ፋኖ ሰራዊት መንግስት ሕዝቡን በመወከል ታላቅ ምስጋና እንዲያቀርብም በአክብሮት እንጠይቃለን። ይሄ አንፀባራቂ ድል ለኢትዮጵያ አገራችን እና ለሕዝቧ ዘላቂ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲኖረው የማድረግ ኃላፊነት በመላ ኢትዮጵያዉያን ትከሻ ላይ የወደቀ ቢሆንም በዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራዉ የአገራችን መንግስት ግን በተለየ ትልቅ ሃላፊነት አለበት። በእኛ እይታ የህወሓት ዋና ዋና መገለጫዎች የነበሩት መሃይምነት፣ ጎስኝነት፣ ሌብነት፣ ትምክህት እና ማን አለብኝንት ናቸው። እነዚህ ባህርያቱ ከፀረ ኢትዮጵያ አጀንዳዉ ጋር ተጣምረው ለአገር እና ለወገን ፋይዳ ያላቸዉን ጉዳዮች ሲያርቅ እና ሲንቅ ኖሯል። አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ይሄንን አይነት ስህተት እንደማይሰራ ተስፋ እናደርጋለን። ከዚህ ተስፋ በመነጨ በህወሓት እጅግ ብዙ መከራ እና ግፍ ከተቀበለው የሐረርጌ ሕዝብ አብራክ የወጣዉ የሐረር ፍትህ እና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ይህንን ማሳሰቢያዊ መግለጫ አውጥቷል። የሚከተሉትን ጉዳዮች መንግስት ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲመለከታቸው፡ ፩. ባለፉት ፴ አመታት የፋሽስት ጣልያን ቅሪት የሆነው ህወሓት በአገራችን ኢትዮጵያ እና በሕዝቧ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ክህደት እንደፈፀመ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚገባ ያዉቃል። በተለይ አገራችን ኢትዮጵያ ታሪኳ በፅሁፍ መዘከር ከጀመረበት ከዛሬ አምስት ሺህ አመታት ወዲህ በጭራሽ ታይቶ እና ተሰምቶ በማይታወቅ ግድየለሽነት እና አቅም ማነስ ምክንያት ከክብር ማማዋ ወርዳ እንድትዋረድ እና ትላንት የተፈጠሩ ጎረቤቶቿ ሳይቀር ብዙ ቀድመዋት እንዲሄዱ ያደረጉበትን አግባብ ንቆ ወይም በይቅርታ ብቻ ማለፍ አይቻልም። ይህ ወንጀለኛ ቡድን እና መሪዎቹ ባሰቸኳይ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ እና ሕጉ የሚፈቅደው ቅጣት ያለምንም ርኅራኄ እንዲወሰንባቸው እንጠይቃለን። ፪. በኢትዮጵያ ምድር ላይ ህወሓት እና ህወሓትን መሰል ኋላቀር እና በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ የሚያራምዱ ኃይሎች በአሸባሪነት እንዲፈረጁ እና በጎሳ እና በሃይማኖት ዙሪያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ ከኢትዮጵያ ወርድ እና ቁመት ጋር ስለማይመጣጠን በሕግ እንዲታገድ እንጠይቃለን! ፫. ለተጨማሪ ግጭት እና ሞት ሊዳርጉ የሚችሉ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ባሰቸኳይ እና በጥንቃቄ እንዲፈቱ እንጠይቃለን። ለምሳሌ የህወሓት ወንበዴዎች ደርግን ይዋጉ በነበሩበት ወቅት በጎንደር ሕዝብ ተጋድሎ ከደርግ እጅ የወጣዉን በቀድሞው አጠራሩ ሰሜን አዉራጃ ይባል የነበረዉና የበጌምድር ታሪካዊ አካል የሆኑትን ወልቃይት፣ ሁመራ አና ጠለምትን በሕገ ወጥ መንገድ የኛ ነው ወደሚሉት የትግራይ ክልል አስገብተዉ ቆይተዋል። ይህንንም ተከትሎ እንኳን ለአይን ለጆሮ የሚቀፍ ግፍ በባለአገሩ ላይ አድርሰዋል። በተመሳሳይ ምንጊዜም የወሎ ክፍለ ሃገር አካል የነበረው የራያ አዉራጃ ወደ ጥንት ክልሉ እንዲመለስ መደረግ እንዳለበት እናምናለን። በዚህ አገባብ በቀድሞዉ ጎጃም ክፍለ ሀገር የመተከል አዉራጃ ከህወሓት ድብቅ አጀንዳ አንፃር ካልሆነ በቀር በቀድሞው ወለጋ ክፍለ ሃገር ከሚገኘው እና አሁን አንድ ላይ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እየተባለ ከሚጠራው ቦታ እና ሕዝብ ጋር አንድ እንዳልሆነ ይታወቃል። በግድቡ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮች እንዳሉ ሆኖ ህወሓት እና ግልገሎቻችው በስፍራው የሰዉን ልጅ በአሰቃቂ ሁኔታ እየፈጁ ያሉት ይሄን ሀቅ ስለሚረዱና ዘርን በማጥፋት አካባቢዉን የራሳቸው የማድረግ ሕልም ስላላቸው እንደሆነ ግልፅ ነው። ባጠቃላይ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ችግሮች ዋና መንሰኤ ህገ መንግስቱ ቢሆንም እና አሱ ሲስተካከል ብዙ ነገር መልክ የሚይዝ ቢሆንም ይሄ ብዙም ከሕገ መንግስት ጋር የማይገናኝ ግን የሰላማችን ዋስትና የሆነ ጉዳይ ባስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግለት እናሳስባለን። ፬. በተለያዩ ክልሎች ውስጥ የተሰገሰጉ እና ከችሎታ እና እዉቀታቸው ይልቅ ጎሳቸው እና ቋንቋቸው ትልቅ ስልጣን እና ጥቅም ያስገኘላቸው ኃይሎች የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዙ መስዋዕትነት ከፍሎ ዛሬ ያገኘዉን ድል እና እረፍት ለማሳነስ እና ለማኮላሸት የተለያዩ አሻጥሮችን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ እንገምታለን። ስለሆነም የዶ/ር አብይ አህመድ መንግስት ይህ ድል የሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲሆን የሚችለዉን ሁሉ እንዲያደርግ እናሳስባለን። የህወሓት ወጥ ሥራ የሆኑ አካላት ለምሳሌ የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ [የሐረሪ ብልፅግና] ህዝቡ በህወሓት መደምሰስ ደስታዉን እንኳን መግለፅ እንዳይችል ከማድረጋቸዉም በላይ ወጣቶችን የኢትዮጵያን ታሪካዊ ባንዲራ ይዛችኋል በሚል ሰበብ ብቻ ሲያስሩ እና ሲያንገላቱ እየታየ ነው። ይሄ አሳፋሪ እና አሳዛኝም ነው። የኢትዮጵያን መለዮ ለባሽ ድል ለማክበር የፖለቲካ ፓርቲዎች ይሁንታ የሚያስፈልግበት አገር ኢትዮጵያ ከዛም ሐረር ብቻ እንደሆነ እያየን ነው። ይሄ የስልጣን ብልግና ልክ ይበጅለት ዘንድ በአፅንኦት እንጠይቃለን። ህወሃትን የታገልነው በያዘው ኋላቀር የፖለቲካ ፍልስፍና እና በኢትዮጵያ ላይ ባደረሰዉ ዉርደት ምክንያት ነው። ከዚህ በኋላም ይህንን አይነት ከዘመኑ ጋር የማይራመድ እና ህዝባዊ ያልሆነ አሰራር እና ተቋም እስከመጨረሻው እንታገላለን!! ፭.. ከሁሉ በላይ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቅቆ እንደሚረዳዉ አንድ መርዛማ ድርጅትን የሚመሩ ድዉያንን በመደምሰስ ብቻ ይሄ ድርጅት ለሰላሳ ዓመታት የረጨዉን መርዝ ማርከስ አይቻልም። በማንነት ቀዉስ የሚሰቃዩት የመርዛማዉ ህወሓት መሪዎች እና አምላኪዎች የረጅም ጊዜ አጀንዳቸው አገራችን ኢትዮጵያን ማፍረስ እና የዘረፉትን ሀብት እና ንብረት ይዘው የየመንደራቸው አዉራ መሆን ነበር። የቃልኪዳን አገር የሆነችው ኢትዮጵያ በኪነ ጥበቡ ተርፋ ነው እንጂ እንደ እነሱ ምኞት እና ተንኮል ቢሆን ኖሮ አገራችንን አሁን ባለችበት ሁኔታ ማግኘት እንደማይቻል ሁላችንም እናዉቃለን። ይህን አይነት ጋጠወጥነት በአገራችን ድጋሚ እንዳይከሰት በዚህ ዘመን ሊደረግ የሚገባዉ ነገር ሁሉ መደረግ አለበት። ህወሓት እና አምላኪዎቹ ከረጅም ጊዜ ግባቸው እኳያ የነደፉትና ለ ፴ አመታት አገራችንን ራቁቷን እንዲያሰቀሯት አመቺ ሁኔታ የፈጠረላቸው እራሳቸው አርቅቀው እራሳቸው ያፀደቁት እና አሁንም ሥራ ላይ ያለው ሕግ መንግስት ነው። ሐፍዴፓ ይሄ ህገ መንግስት የአገሪቱ የበላይ ሕግ እስከሆነ ድረስ ህወሃት ተሸንፏል ብሎ አያምንም። ይሄ ህገ መንግስት የህወሓት እና የህወሓት የጡት ልጆች ብቻ ነው። በገዛ አገራችን ባዕድ ለተደረግን በርካታ ሚሊየን ኢትዮጵያዉያን ሕገ መንግስቱ እዉቅና እንኳን አይሰጠንም። የማያዉቀንን ህገ መንግስት እኛ እዉቅና ልንሰጠው እንችልም። ስለዚህ የዶ/ር አብይ አህመድ መንግስት ባስቸኳይ የህገ መንግስት ክለሳን አስፈላጊነት እና አካሄድ የሚመራ ኮሚቴ ባስቸኳይ እንዲያቋቁም እና ህገ መንግስት የሚከለስበትን ቅድመ ሁኔታ እንዲያመቻች እንጠይቃለን። ሕግን ከማስከበሩ እና ህወሓት ወለድ የሆነዉን ህገ መንግስት ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን የሚመጥን ከማድረግ ጎን ለጎን የሚከተሉትም ጉዳዮች ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብለን እናምናለን፦ ፩. ትዉልድን ከአለም አቀፋዊ አመልካከት ይልቅ የጎሳ እና የጎጠኘነት ስሜት ይዞ እንዲያድግ የሚያደርግ የትምህርት ፖሊሲ አንድ የኢትዮጵያን ትዉልድ እንዳጠፋ ለማንኛዉም ጤነኛ ኢትዮጵያዊ ግልፅ ነው። የህወሓት መሪዎች ከነበረባቸው ፀፀት እና የበታችነት ስሜት በመነሳት የትምህርት ጥራት ብሎም አዉቀት ላይ ትልቅ በደል ፈፅመዋል። ከዚህ የተበላሸ ስብዕና የወጣው የትምህርት ፖሊሲ ከእዉቀት ይልቅ አንድ ቦታ ላይ መወለድ፣ እንድ ቋንቋ መናገር ወይም አድርባይነት የበለጠ ይጠቅማል ብሎ የሚያስብ ትዉልድ እንዲፈጠር አድርጓል። ትዉልድ መገንባት ላይ ያተኮረ እና ከፖለቲካ አጀንዳ የፀዳ የትምህርት ፖሊሲ የትምህርት ስርዓት ዝግጅት እንዲጀመር እንጠይቃለን። ፪. የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለፉት ፴ አመታት ከእዉነተኛ ታሪክ ይልቅ በፀረ ኢትዮጵያዊነት እና በፀረ አንድነት አጀንዳ የተገመደ ትርክት ሲጋት ኖሯል። ቋንቋን፣ ሃይማኖትን እና አሰፋፈርን የማነንት ዋና መገለጫ እና የታሪክ አንጓ በማስመሰል እና የፖለቲካ መሳሪያ በማድረግ ኢትዮጵያዉያንን አንድ ከሚያደርጓቸው እልፍ ጉዳዮች ይልቅ ጥቂት እና ስሜታዊ የሚያደረጉ ልዩነቶቻቸው ላይ እንዲያተኩሩ ተደርገዋል። በዚህም ምክንያት የተወሰነ ቋንቋ ተናጋሪ እና ሃይማኖት ተከታይ ወገን የህወሓት ባዕድ አምልኮ መስዋዕት ሲደረግ ኖሯል። የኢትዮጵያ መንግስት ይሄን ወቅት ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ምሁራን እንጂ የፖለቲካ ካድሬዎች የአገራችንን እና የህዝባችንን ታሪክ የሚያስተምሩበት እንዳይሆን ማድረግ አለበት። ኢትዮጵያውያን በጎሳ እና በነገድ ሊከፋፈል የማይችል ማንነት ያለን እንደሆንን በግልፅ እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ አሁን ያለውም ሆነ ያለፈው ትዉልድ የሚማርበትን ሁኔታ መንግስት እንዲያመቻች እንጠይቃለን። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛ መስዋዕት ከፍሎ የፋሺስት ጣሊያን አስተምህሮ ቅሪት የሆነዉን ህወሓትን በመደምሰስ እጁ ያስገባዉን ወርቃማ ዕድል በአግባቡ እና በብቃት መጠቀም የመንግስት ኃላፊነት ስለሆነ ይህን ኃላፊነቱን በታማኘንት እና በቁርጠኘት እንዲወጣ እያሳሰብን የሐረር ፍትህና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲም ሐረር/ሐረርጌንም ሆነ መላዉ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መንግስትን ለማገዝ ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እንገልፃለን። የኢትዮጵያ አምላክ አገራችን ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ይባርክ!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply