
ህወሓት ከአፋር ክልል ሙሉ በሙሉ ለመውጣት ያልተገደበ ሰብዓዊ እርዳታ አሰራር መዘርጋትና የተቋረጡ መሰረተ ልማት አገልግሎቶች መመለስን ጨምሮ የተወሰኑ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠ። የትግራይ ኃይሎች በአፋር ክልል የመቆየታቸው ሁኔታ ያለውን የጸጥታ ስጋት ለማስወገድ እንደሆነ የገለጸው ህወሓት ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ በመርህ ደረጃ “ከአፋር ክልል ለመውጣት ቁርጠኞች ነን” ሲሉ የህወሃት ቃለ አቀባይ ጌታቸው ረዳ በትናንትናው ዕለት በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።
Source: Link to the Post