You are currently viewing ህወሓት የወሰዳቸውን ቤተሰቦቻችን የፌደራል መንግሥት ያስለቅቅልን ሲሉ የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች ጠየቁ።              ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም                       አሻ…

ህወሓት የወሰዳቸውን ቤተሰቦቻችን የፌደራል መንግሥት ያስለቅቅልን ሲሉ የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች ጠየቁ። ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም አሻ…

ህወሓት የወሰዳቸውን ቤተሰቦቻችን የፌደራል መንግሥት ያስለቅቅልን ሲሉ የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች ጠየቁ። ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በፌደራል መንግሥትና በህወሓት ሃይሎች ተቀስቅሶ በነበረው የሰሜኑ ጦርነት ወቅት በህወሓት ሃይሎች የተወሰዱ የቤተሰባችን አባላትን የፌደራሉ መንግሥት ያስመልስልን ሲሉ በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን ነዋሪዎች ጠይቀዋል። በኹለተኛው ዙር ጦርነት፤ የአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ሙሉ ለሙሉ በትግራይ ክልል ሃይሎች በቁጥጥር ሥር ውሎ በነበረት ወቅት፤ በተለይም የህወሓት ሃይሎች ወልዲያንና አካባቢዋን ሲቆጣጠሩ በአካባቢው የሚኖሩ በርካታ ሰዎችና አርሶአደሮች <<የቀድሞው ሰራዊት አባል ወይም ሚሊሻ ናችሁ።>> በሚል ከጥቅምት 23 /2014 ጀምሮ በወደ መቀሌ እየተጫኑ እንደተወሰድ የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ ቤተሰቦቻቸው እስካሁን የት እንደሚገኙ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በሰሜን ወሎ ዞን ብቻ ከ460 በላይ ሰዎች ተወስደዋል የሚሉት ነዋሪዎቹ፤ በትግራይ ክልል ሳምሪ በተባለ ቦታ እንደታሰሩ የሰሙ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን የት እንዳሉ መረጃ ማግኘት ባለመቻላቸው የፌደራል መንግሥት እነዚህን ሰዎች እንዲያስለቅቅላቸው፣ በህይወት ከሌሉ ደግሞ የሉም እንዲላቸው በተማጽኖ ጠይቀዋል። በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ ዙሪያ በጉባ ላፍቶ ወረዳ ደቦት እና በቅሎ ማነቂያ ተብሎ በሚጠራ ሥፍራ ሦስት ወንድማማቾችና ኹለት ጎረቤቶች በአጠቃላይ ከአንድ አካባቢ አምስት ሰዎች እንደተወሰዱ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ቤተሰቦች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። ከ460 በላይ የሚሆኑ የሰሜን ወሎ ዞን ነዋሪዎችን <<የቀድሞው የሚሊሻ አባላት ናችሁ፣ ለፌደራል መንግሥት መረጃ እያቀበላችሁ ነው።>> በማለት ከቤታቸው በተቀመጡበት አስረው በመውሰድ በአውንተገኝ ወረዳ ባባስዓት ተብሎ በሚጠራ ቀበሌ ለትንሽ ቀናት ካቆዩዋቸው በኋላ ታህሳስ 7/2014 ወደ መቀሌ እንደወሰዷቸው ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት። <<አባቶቻችን በህወሓት ሃይሎች በመወሰዳቸው አርሶና ሸምቶ የሚያበላን በማጣታችን ለችግር ተጋልጠናል።>> የሚሉት የታሳሪዎቹ ልጆች፤ በህይወት ስለመኖራቸው እንኳን ማረጋገጥ እንዳልቻሉ አስረድተዋል። የሰሜን ወሎ ነዋሪ የነበሩት እነዚህ ነዋሪዎች በህወሓት ሃይሎች መታሰራቸውን እና የት እንዳሉ መንግሥትም ሆነ ቀይ መስቀል እንደማያውቁ የተናገሩት የታሳሪ ቤተሰቦች፤ <<ለቀይ መስቀል የታሰሩትን ሰዎች ሥም እና አድራሻ በተደጋጋሚ ብናስመዘግብም እስካሁን ሊያገኟቸው እንዳልቻሉ ነግረውናል>> ሲሉ አክለዋል። ሥሙን መጥቀስ ያልፈለገ የትግራይ ሰራዊት አባል እንደሚለው ከሆነ <<በወቅቱ በሰሜን ወሎ አካባቢ በርካታ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አውለን ነበር፤ በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ አናውቅም>> ሲል ለአዲስ ማለዳ ገልጿል። የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች <<መንግሥት እነዚህን ሰዎች አፈላልጎ እንዲያስለቅቅልን፣ በሕይወት ከሌሉም ደግሞ የሉም እንዲለን እንፈልጋለን>> ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply