You are currently viewing ህወኃት ትግሌ ሀገር መሆን ነው አለች! የመቀሌው ህወሃት እና ፕሪቶሪያ የተደራደረው ህወሃት አንድ ነን ብሏል። ህወሃት አልተከፋፈለም፣ አንድ ነን  ብሏል። ጌታቸው ረዳ ድርድሩን ህወሃት አያው…

ህወኃት ትግሌ ሀገር መሆን ነው አለች! የመቀሌው ህወሃት እና ፕሪቶሪያ የተደራደረው ህወሃት አንድ ነን ብሏል። ህወሃት አልተከፋፈለም፣ አንድ ነን ብሏል። ጌታቸው ረዳ ድርድሩን ህወሃት አያው…

ህወኃት ትግሌ ሀገር መሆን ነው አለች! የመቀሌው ህወሃት እና ፕሪቶሪያ የተደራደረው ህወሃት አንድ ነን ብሏል። ህወሃት አልተከፋፈለም፣ አንድ ነን ብሏል። ጌታቸው ረዳ ድርድሩን ህወሃት አያውቀውም ብሏል። እኔ የተደራደርኩ የትግራይ መንግስትን ወክየ ነው ብሏል። ነገሩ አስገራሚ ሆኗል። ሕዳር 7 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከፌዴራል መንግሥት ጋር በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተፈረመው የሠላም ስምምነት ሕወሓትን ወክለው የፈረሙት ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ፤ የትግራይን ሕዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት በፖለቲካ ውይይት የማረጋገጥ ዕቅድ መያዛቸውን ይፋ አድርጓል።፡ አቶ ጌታቸው ይህን ያሉት በጦርነቱ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብና በግድያ ሞተው፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶችም የፆታዊ ጥቃት ሰለባ ሆነውና የተለያዩ ጥሰቶችም ተፈጽመው ከዚህ ሁሉ በኋላ ‹‹ትግራይ ምን አተረፈች›› በሚል ከቢቢሲ ለተሰነዘረላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነው፡፡ በምላሻቸው ‹‹ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ የለም›› ያሉት ጌታቸው፤ ‹‹ህልውናችንን ለማረጋገጥ የሚያስችል አቋም ይዘን ትርፍ ሳይሆን ቢያንስ እንካሳለን ብለን እናምናለን›› ሲሉ ከድርድሩ በኋላ ለማግኘት ያለሙትን ገልጸዋል፡፡ የዜና ተቋሙ ‹‹የትግራይ ካሳ ምን ይሆናል›› በሚል ላስከተለው ጥያቄ የሕወሓት ዋና ተደራዳሪው ሲመልሱ፤ ‹‹ሕዝቡ ምኞቱን እና ፍላጎቱን፣ ወይ አገር ይሁን ወይ የሆነው ይሁን እኔ መወሰን ስለማችል፥ ሙሉ በሙሉ የሚያረጋግጥበት ሁኔታ መፍጠር ነው ነው ካሳው›› ብለዋል፡፡ አያይዘውም ‹‹ይህን ለማድረግ በሰላማዊ መንገድ ወይም በጦርነት የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን፤ የትግራይ ሕዝብ ይህን ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም›› በማለት አክለዋል፡፡ ጨምረውም ከፌዴራል መንግሥት ጋር በነበረው ድርድር የተቀበሉት ‹‹የተኩስ አቁም›› መሆኑን በመጥቀስ፤ ‹‹ተኩስ ከቆመ በኋላ የፖለቲካ ውይይት ይቀጥላል። በፖለቲካ ውይይት የትግራይን ሕዝብ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ካላረጋገጥኩኝ ተኩስ ለማቆም ስለወሰንኩ ብቻ የሚቀበለኝ ሰው ይኖራል›› ወይ ሲሉ ጥያቄውን በጥያቄ መልሰዋል፡፡ አቶ ጌታቸው ‹‹የትግራይ ሕዝብ እና የትግራይ ሠራዊት እኔ እንደፈለግኩ የምነዳው አይደለም›› ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡ ፌዴራል መንግሥትም ይሁን ዓለም አቀፍ መንግሥታትም ይሁኑ ማንም ይሁን የትግራይን ሕዝብ ፍላጎት ከማሟላት ውጪ አማራጭ ያለው አይመስለኝም›› ያሉት ጌታቸው፤ ‹‹ዋናው ተኩሱ ይቁም፣ የትግራይ ሕዝብ እርዳታ ይቅረብለት፣ አገልግሎት ያግኝ፣ በፖለቲካዊ ውይይት በሰላማዊ መንገድ የሚፈታ ነገር ካለ እናያለን፤ መፍታት ካልተቻለ ትጥቅ ይፍታ ስላልኩት የሚፈታ ሠራዊት የለም›› ብለዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተገናኘ ጦርነቱ አብቅቷል ወይ የተባሉት ጌታቸው፤ እንዳላበቃ በመግለጽ፤ ‹‹ተኩስ አቁመናል፤ ጦርነቱ አለቀ ማለት አይደለም›› ሲሉ መልሰዋል፡፡ ለድፍን ሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ የቆዩት የፌዴራል መንግስት እና ሕወሓት ጥቅምት 23፣ 2015 በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል፡፡ በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት የመንግስትና የሕወሓት የጦር አዛዦች በተኩስ አቁም አፈፃፀም፣ በጦር ስራዊት አሰፋፈር እንዲሁም በትጥቅ መፍታት ጉዳይ ላይ በተመሳሳይ ባለፈው ቅዳሜ ስምምነቱን ለመተግበር ቁርጠኝነታቸውን በፊርማ አረጋግጠዋል፡፡ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረትም የፌደራል መንግሥት መቀሌን ተረክቦ በከተማው ውስጥ እና ዙሪያ ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያ ያስፈታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ አሁን ያለው የሕወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር እንደሚቋቋምም ሠፍሯል፡፡ በሚዋቀረው ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥም የትግራይን ሕዝብ የሚወክል አካል ይሳተፋል፤ በትግራይ የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የማኅበራዊ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ ሁኔታዎች ያመቻቻል፤ ተግባራዊነታቸውን እንደሚያረጋግጥም ስምምነቱ ያመለክታል፡፡ ጌታቸው ረዳ ጦርነቱ ሊቀጥል ይችላል፣ ህወሃት አልተደራደረም፣ የኛ ዓላማ የትግራይን ነፃ ሀገርነት መመስረት ነው ያሉት የስምምነቱን ፍሬነገር ሁሉ በመቃረን ነው ተብሏል። በስምምነቱ መቃረን፣ ማፈንገጥ፣ የጥላቻ ንግግር ማውራት እንደማይቻል ሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች ተነጋግረው ነበር። በሌላ መረጃ ህወሃት ተቆጣጥሮት ባለው ሰላሳ ከመቶ በሚሆነው የትግራይ ክልል ወጣቱን ለውጊያ እየሰበሰበ፣ ምሽግ እየቆፈረ፣ ለሌላ ዙር ጦርነት እየተዘጋጀ ስለመሆኑ ለሳተናው የደረሱ መረጃዎች ያሳያሉ። ህወሃት ከሰላም ይልቅ ጦርነትን የመረጠ ይመስላል። በትናንትናው የፓርላማ ውሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጦርነት የሚሰብኩ የመሳሪያ ደላሎች ናቸው። ስምምነቱ እንዲሳካ እንጥራለን ብለው ነበር። ህወሃት ግን ከዚህ በተቃራኒ የአማራ ፋኖ በአድዋ፣ በአክሱም ገብቶ እየተዋጋ ነው ሲል ትናንት መግለጫ አውጥቷል። ፋኖ አክሱም ገብቷል እያሉ የህወሃት ካድሬዎች። የአማራ ልዩ ሀይልም ሆነ ፋኖ ወደ ትግራይ ክልል እንዳልገቡ ሲነገር ቆይቷል። አሜሪካ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች። ስምምነቱ በፍጥነት ተግባራዊ የማይሆን ከሆነ ማዕቀብ እጥላለው ብላለች። የኤርትራ ሰራዊትም በፍጥነት ይውጣ ብላለች። አሜሪካ ያሰበችው ማዕቀብ የአሁኑ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ እንደ ኤርትራ ከዓለም የሚነጥል መሆኑ ተደርሶበታል። ይህ የአሜሪካ ከባዱ ማዕቀብ ነው ተብሏል። አልተደራደርኩም የሚለው ህወሃት ስምምነቱ እስካሁን ፍሬያማ አልሆነም በሚል ነገር እያቃጣጠለም ይገኛል። የስምምነት ሰነዱ የሚለው በህወሃት እና በመንግስት ቢልም፣ ህወሃት የፈረመበትን ወረቀት እንኳን ክዶታል። የናይጀሪያው የቀድሞ ፕሬዜዳንት ኦሊሶንጎ ኦባሳንጆ ዛሬ መቀሌ ናቸው። ከነጌታቸው ረዳ ጋር ከካይሮ ወደ መቀሌ አምርተው ከደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጋር ተወያይተዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋርም ስለመወያያታቸው ተገልጿል። ነገርግን ስምምነቱን በፍጥነት ተግባራዊ ለማድረግ ገና ቅድመ ሁኔታው በርካታ ነው ስለማለታቸው እየተዘገበ ነው። ይሄን ተከትሎም ይመስላል አሜሪካ ቀጣይ ጉዞየ ማዕቀብ ነው ያለችው። ኢሳያስ አፈወርቂ ደግሞ እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም ሲሉ የህወሃትን እባብነት አስረግጠው ተናግረዋል። ነገሮች እንደገና እየሻከሩ ይገኛሉ። ዘገባው የሳተናው ሚዲያ ነው። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply