ህዝቡ ልማቱን እያከናወነ አካባቢውን ነቅቶ መጠበቅ አለበት- አቶ ተመስገን ጥሩነህ

ህዝቡ ልማቱን እያከናወነ አካባቢውን ነቅቶ መጠበቅ አለበት- አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ህዝብ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተሰናባቹ የክልሉ ርዕስ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ አሳሰቡ።
አቶ ተመስገን ጥሩነህ በዛሬው የምክር ቤት ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት “ትህነግ ባለፉት ዓመታት አሳፋሪ ድርጊቶችን ሲፈፅም ቆይቷል፤ አሁን ላይ ደግሞ የባሰውን አስነዋሪ ድርጊት እያከናወነ ይገኛል” ብለዋል።
ትህነግ የኢትዮጵያ ህዝቦች እርስ በእርሳቸው ጥርጣሬ ውስጥ እንዲወድቁ፣ መከፋፈልና ዘረኝነት እንዲነግስ አልሞ ሲሰራ ቆይቷል ያሉት አቶ ተመስገን፤ በዚህም የተነሳ በሃገሪቱ ታርክ ታይቶ በማይታወቅ አግባብ በአሁኑ ወቅት ብዙ የተወሳሰቡና የተመሰቃቀሉ ችግሮች እንዲፈጠር መደረጉን ገልፀዋል።
ችግሩ በረጅም ጊዜ የተፈጠረና ታስቦበት ሲሰራ የቆየ በመሆኑ በአንድ ጀምበር መፍታት እንደማይቻልም ተናግረዋል።
“ችግሩን ለመፍታት ዋናውን የችግሩን ምንጭ ማጥፋት ወሳኝ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማድረቅ በተቀናጀ አግባብ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል”ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
“ቀደም ሲል በትህነግ ጽንፈኛ ቡድን ሲበደል የኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ላይ እራሱ በከፈተው ጦርነት በጋራ በመቆሙ ድል እየተነሳ ነው” ብለዋል።

The post ህዝቡ ልማቱን እያከናወነ አካባቢውን ነቅቶ መጠበቅ አለበት- አቶ ተመስገን ጥሩነህ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply