ህዝቡ በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻችንን በመርዳት በዓሉን እንዲያሳልፍ ጥሪ ቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸዋ…

ህዝቡ በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻችንን በመርዳት በዓሉን እንዲያሳልፍ ጥሪ ቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

ህዝቡ በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻችንን በመርዳት በዓሉን እንዲያሳልፍ ጥሪ ቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ህዝቡ በአገራችን በአንዳንድ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች፣ በኮኖርና ወረርሽኝና በተለያዩ ምንያቶች ኑሯቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ወገኖቻችን በመርዳት የገና በዓል እንዲያሳልፍ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ ጥሪ አቀረቡ። አቶ ኦባንግ በተለይ፣ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት ፣ ከዚህ በፊት በበዓላት ጊዜ ድጋፍ የሚደረገው በአመዛኙ ኑሯቸውን ጎዳና ላይ ላደረጉና ለአቅመ ደካማ አረጋውያን መሆኑን ጠቁመው፣ አሁን ግን በመተከል፣ በደቡብ፣ በኦሮሚያ እና በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰቱት ግጭቶች፣ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ እንዲሁም በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ሰዎች በርካታ በመሆናቸው ህብረተሰባችን ከምንጊዜም በላይ የወገን አለኝታነቱን የሚገልጽ የድጋፍ እጁን እንዲዘረጋ ጠይቀዋል። ህብረተሰባችን በፖለቲካ አመለካከቱ፣ በዘር፣ በሃይማትና ብሔር ሳይለያይ፣ ብቻ እንደ ሰው በማሰብ አቅም በፈቀደ መጠን የሚበላ፣ የሚጠጣና የሚለበስ በማቅረብ ለችግር የተጋለጠ ማንኛውም ሰው ሊረዳ እንደሚገባው አመልክተዋል። አገራዊና ወገናዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ጀርመን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር 220 ሺ ብር መሰብሰባቸውን ጠቁመው፤ ብሩ በግጭት ምክንያት በተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች እንደየፍላጎታቸው የተለያዩ አልባሳትና ምግቦች ገዝቶ ለመላክ ፍላጎታቸውን የመለየት ሥራ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። ከአገር ውስጥም ከተለያዩ ድርጅቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ባለሀብቶች ድጋፎችን ለመሰብሰብ እንቅስቃሴ መጀመራቸውና የተሰበሰቡ ድጋፎችም ከተፈናቃዮች በተጨማሪ በመዲናይቱ በችግር ላይ ለሚገኙ ህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚውል ገልጸዋል። በዚህ የተቀደሰ ተግባር ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ወገኖች በሩ ክፍት መሆኑንም አመልክተዋል። “በአገራችን አንዳንዶች ለአማራጭ ብለው ዶሮ፣ በግ፣ፍየልና በሬ ሲገዙ ማየት በጣም ያስደስታል፤ አልባሳትና ሌሎች የቅንጦት ዕቃዎችም መጠቀም እንደዚያው። አሳዛኙ ገጽታው ግን፣ ምንም የሚላስ የሚቀመስ አጥቶ የሚማቅቅ ኢትዮጵያዊ ማየት ነው” ብለዋል። ኢ ፕ ድ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply