ህዝቡ ያለበትን ህመም ከማባባስ ይልቅ መድሃኒት ለመሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰራት እንዳለባቸው ኢዜማ ጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ የምርጫ ስትራቴጂ እና ማኔጀመንት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ከውሰር ኢድሪስ ለአሐዱ እንደገለፁት በዚህ ሀገር ሁኔታ ያልተቀየረው መንግስት ብቻ ሳይሆን ተፎካካሪ የሚባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ጭምር ናቸው ብለዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች እራሳችን አልተቀየርንም ያሉት ከውሰር፤ ለህዝቡ ችግር ከመንገር ይልቅ ተስፋ ወደ መስጠቱ መምጣት አለብን የሚል ሀሳባቸውን ለጣቢያችን አካፍለዋል፡፡ያለውን ትንሽ ተስፋም ቢሆን በመጠቀም ለህዝብ አማራጭ መንገዶችን ማሳየት ያስፈልጋል ያሉት ከውሰር ፓርቲዎች ህዝቡ ያለበትን ብሶት ደግሞ ደጋግሞ ከመግለፅ ይልቅ መድሃኒት ወደ መሆን መምጣ አለባቸው ብለዋል፡፡ኢዜማ ምርጫው በዘንድሮው ዓመት መካሄድ አለበት ከሚሉት ወገን ይመደባል፡፡

ጥር 07/2013

አሐዱ ሬዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply