ህዝባችን ተውት! ንጋቱ አስረስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለኑሮ መደጎሚያ መንግሥት የሚከፍላቸው የፌስቡክ መንደር ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል ። እነዚህ ሰዎች ሌላ ፖለቲካ የመስራት አቅም ስሌላቸው ተ…

ህዝባችን ተውት! ንጋቱ አስረስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለኑሮ መደጎሚያ መንግሥት የሚከፍላቸው የፌስቡክ መንደር ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል ። እነዚህ ሰዎች ሌላ ፖለቲካ የመስራት አቅም ስሌላቸው ተግባራቸው ሁሉ ስድብ ነው። የሚሳደቡት ደግሞ ህዝብን ነው። በጠቅላይ ግዛት መድበው ህዝብን ይሰድባሉ። አላማቸው ማበላሸት ነው። መንግሥትም የሚከፍላቸው ህጋዊ ባልሆነ የሙያ ቅጥር ህዝብን ለሚያበጣብጡበት ነው። በርግጥም አንዳንዶቹ በህወሓት ኢህአዴግ ዘመን ቅቤ አንጓች ፣ አፋሽ አጎንባሽ የነበሩ ናቸው። ዛሬም እንደትናንቱ እነዚህ ሰዎች ከፖለቲከኞች በባሰ መንገድ ለህዝባችን እዳ ናቸው። የአማራ ጉልበቱ አንድነቱ ላይ መሆኑን የሚያውቁ ሰዎች በሚነግሯቸው አካሄድ የህዝባችን አንድነት ለማበላሸት ሌት ከቀን የሚለፉ ናቸው። የአማራ ህዝብ ፖለቲካ ለአለፉት 60 አመታት የተበከለው በእንደነዚህ አይነት የግል ጉዳያቸውን ብቻ በሚያሳድዱ ተስፋ ቢስ ሰዎች ምክንያት ነው። አሁን የምላችሁ ህዝባችንን ተውት በውስጡ ሁናችሁ አትበጥብጡት። በጣም የሚያሳዝነው ባለፉት ቀናት በጎጃም ህዝብ ላይ ከ4000በላይ ሰዎች ታፍነዋል፣ ገበሬው በዘር ወቅት ሥራ እንዳይሰራ እየተደረገ ነው፣ በዚህ ምክንያት በሚቀጥለው አመት ከፍተኛ ርሃብ እንዳይከሰት ወረራውን አቁሙ፣ ንፁሃንን አትግደሉ፣ ህፃናትን አትግደሉ፣ አትሰሩ፣ ሰው መዳኘት ያለበት ህግን ተከትሎ እንጅ በወታደራዊ አፈና አይደለም የሚሉ ጥያቄዎች በርክተው ነበር። ከዚህ በኋላ የደቡብ ጎንደር አስተዳደር ከ700 በላይ ሰዎችን አስሬያለሁ የሚል መግለጫ አወጣ። በጣም የሚያሳዝነው ይህ ነው። ከዛ አንዱ ተነስቶ እኛም ብዙ አስረናል አትጠይቁ የሚል መከራከሪያ አመጣ። ለመሆኑ የደቡብ ጎንደር ሰውስ ቢሆን ለምን ያለጥፋቱ ይታሰራል ? ይህ ጥያቄ እኛም ብንታሰርም ምንም አላልንም በከንቱ አትጩሁ ለሚሉት ነው። ሰው በጥፋቱ ከሆነ በህግ ሥርዓት ነው መጠየቅ ያለበት ስንል ለሁሉም እንጅ አንድ የሆነን ህዝብ መከፋፈል ፖለቲካዊም ሆነ ሌላ ጥቅም የለውም ። ከየተለያዩ የጎጃም አካባቢ የሄዱ ታፋኞች ጋይንት መታሰራቸው ይነገራል ። ርቀው መሄዳቸው አግባብ ባይሆንም የጋይንት ሰዎች ግን ወንድም ና እህቶቻቸውን እንደሚንከባከቡ ተስፋ አደርጋለሁ ። ከአሉበት ሄዶ መጠየቅ ወንድማዊና እህታዊ ተግባር ነው። ተከፋዮችም ሆናችሁ ፖለቲከኞች ህዝባችን ተውት። አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ

Source: Link to the Post

Leave a Reply