ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ከገዢው ፓርቲ ብልጽግና ጋር ድርድር እያካሄዱ ነው መባሉን ህወሃት አስተባበለ።ፓርቲው በፌስቡክ ማኅበራዊ መገናኛ ገጹ ዛሬ ባሰራጨው አጠር ያለ መግለጫ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/F1EuWw3GTtadku7R5A3sIqd7FEkFX3P-9zjsL4SySqwC60hks8GUDF9qeTNR6CAp_L3r5hTrOh00lSF2b54zm8nGIvihQCh7_AtAY9NJVlZFCm99JKBbu1nzkcdIH4KBTf6ZF7loB5aB7lUlXQacN5v-JpcvFmTfp9LH7ORJSjplXQqm0YHWUWmRWBmdYHQCplum51i2UWE4lDBbEdRybLgmjx_24COBu3rTRwcs6UlWoeOwnIDJlSkzAuk12Sja11q4Ypm-CBeQpTEe3qmxFZoRtFYeZmbwE4nr6ZV85Vjz9ceH9dKujNjs4RIrikhB6rzF972mgmJ3i8ynGywdCw.jpg

ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ከገዢው ፓርቲ ብልጽግና ጋር ድርድር እያካሄዱ ነው መባሉን ህወሃት አስተባበለ።

ፓርቲው በፌስቡክ ማኅበራዊ መገናኛ ገጹ ዛሬ ባሰራጨው አጠር ያለ መግለጫ ህወሃት ከብልጽግና ጋር የሚያደርገው ድርድር ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ለማስፋትና ለማጠናከር ያለመ ነው ብሏል።

ህወሃትና እና ብልጽግና መሠረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት እንዳላቸው ያመለከተው ፓርቲው ልዩነታቸው እንዳለ ሆኖ ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች እንዳሉም አመልክቷል።

እንዲያም ሆኖ «ህወሃት ከብልጽግና ጋር ለመቀላቀል ንግግሮች ተጀምረዋል የሚባለው አባባል ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው» ሲል ይህን በተመለከተ የሚናፈሰውን መረጃ አስተባብሏል።

ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply