ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (1975 ተወልደ-2020 ሞተ)፤ ወያኔ ጁንታ በአዴ አብ ጉድጎድ ተቀበረ!!! ሚሊዮን ዘአማኑኤል

መንግሥት ይሄዳል ይመጣል፣የሃገር መሪ ይሾማል ይሻራል፣የሃገር መከላከያ ሠራዊት ዘላለም ይኖራል!!!

‹‹ደግሞ ማወቅ ማለት…..

ከውጭ ያለውን ሄዶ ከመፈለግ

ከውስጥ የበራውን፤ እንዲወጣ ማድረግ….›› ገብረክርስቶስ ደስታ

‹‹በምዕራብ የጦር ግንባር ሁሉም ነገር ፀጥ  እረጭ አለ›› ብሎ በ1928 እኤአ የፃፈው ጀርመናዊው ኤሪክ ማሪያ ሪማርኪ ነበር፡፡ በዓለማችን የጦርነት ታሪክ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ታሪክ ነው፣ ጦርነት ማለት በእውነት ምን ማለት እንደሆነ መፅሃፉ ፍንትው አርጎ ያሳያል፡፡ የጀርመን ናዚ ፓርቲ  መንግሥት መፀሃፍቶቹን ሠብስቦ በአደባባይ አቃጠላቸው፣ መፅሃፉ  ፀረ ጀርመን፣ ፀረ ጦርነት፣ ፀረ አርበኞችና የጀርመኖችን ጦርነት የመዋጋjት ችሎታ ያጣጣለ ነው በማለት ናዚዎች አቃጠሉት፣ ጸሃፊውም ከጀርመን ወደ ሌላ አገር ተሰደደ፡፡  አሪፍ ተርጎሚ ቢያገኝ በተለያዩ የሃገሬ ቌንቌዎች ተተርጉሞ ባይ ልቤ በደስታ ይዋኛል፡፡ ፊልሙንም በቴሌቪዝን ቢያሳዩት ስለጦርነት ትምህርት ይሰጣልና አስቡበት፡፡ All Quiet on the Western Front by Erich Maria Remarque’s novel (1928). Erich Maria Remarque’s famed 1928 novel All Quiet on the Western Front was deemed degenerate, or anti-German, and banned in Germany with the rise of the Nazi Party. … The Nazis felt the novel was anti-war and unpatriotic, and claimed that its realistic portrayal of trench warfare made Germans look ‘weak’.

ብሔራዊ የሃገር መከላከያ ሠራዊት

  • ወያኔ የሃገር ክህደት ወንጀል፣የሽብርተኛነት በዘር ማጥፋት ወንጀል (ጆኖሳይድ) ተጠያቂ ነው፡፡

መንግሥት ይሄዳል ይመጣል፣ የሃገር መሪ ይሾማል ይሻራል፣ የሃገር መከላከያ ሠራዊት ዘላለም ይኖራል፡፡ የህዝቦችም ግንኙነት ዘወትር ህያው ነው፡፡ ኢትዮጵያን የፌዴራል ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት  የመከላከያ ሠራዊቱ መርሆዎች ‹‹የመከላከያ ሠራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኃን ያከናውናል፡፡›› ይላል አንቀጽ 87 ቁጥር 5፡፡  ወያኔ ያወጣውን ህገ መንግሥት በመሻር በጥቅምት 24 ቀን 2013ዓ/ም የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ትህነግ) የትግራይ ክልል የጦር አበጋዞች መንግስት ዶክተር ደብረፂዮን ገብረማርያም በትግራይ ውስጥ የሚገኘውን ኢትዮጵያን የፌዴራል መንግሥት የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ከወያኔ የፖለቲካ ድርጅትን እንዲደግፍ በማስገደድ በሠራዊቱ ላይ የመሣሪያ ጥቃት በመፈፀም የአማራ ተወላጅ ወታደሮችን በመግደል፣ ሰባት ሽህ የሠራዊቱን አባላት በማገት፣ የሃገሪቱን የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በመዝረፍ የተራ ወንበዴ ሥራ በመስራት ህገመንግሥቱን ጥንብ እርኩሱን አውጥተውታል፡፡ ወያኔ በዚህ ሥራው የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ላይ የሃገር ክህደት ወንጀል ፈጽሞል፡፡ ወያኔ የሽብርተኛነት ወንጀል በመፈጸም ብዙ ወታደሮችን በመግደል፣ ሰባት ሽህ ወታደሮች በማገት፣  የእዙን ከባድ መሣሪያዎች በመዝረፍ ወንጀል ተጠያቂ ነው፡፡ ወያኔ በዘር ማጥፋት ወንጀል (ጆኖሳይድ) በተለይም በማይካድራ ከስድስት መቶ አማሮችን በአስቃቂ ሁኔታ በስለት በማረድና በጅምላ መቃብር በመቅበር  ወንጀል ተጠያቂ ናቸው፡፡

  • ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በሽብርተኛነት ተፈርጆ፤ እንደ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) በህግ መተገድ አለበት!!!

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (Workers’ Party of Ethiopia) ኢሠፓ በግራ ዘመም የማርክሲስት ሌኒኒስት የኮምኒስት ርዕዮት ተከታይነት ሴፕቴምበር 12 ቀን 1984 እኤአ በኢትዮጵያ ምድር በሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማርያም ተመሰረተ፡፡ ኢሠፓ ከሰባት ዓመታት ቆይታ በኃላ በህወሓት/ኢህአዴግ ተሸንፎ  በሜይ 21 ቀን  1991እኤአ በህግ ታገደ፡፡   የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ በህግ ታገዱ፣ የመምረጥና የመመረጥ መብታቸው ታገደ፡፡  ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ፤ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (Tigray People’s Liberation Front) በግራ ዘመም የማርክሲስት ሌኒኒስት የኮምኒስት ርዕዮት ተከታይነት በፌብሪዋሪ 18 ቀን 1975 እኤአ በኢትዮጵያ ምድር በደደቢት በርሃ ተመሠረተ፡፡  ህወሓት በሊቀመንበር መለስ ዜናዊ ሃያ ሰባት ዓመታት አገዛዝ ቆይታ በኃላ በህወሓት/ኢህአዴግ ተሸንፎ  በኖቨምበር  24 ቀን  2018 እኤአ በህግ ሊታገደ ይገባል እንላለን፡፡  ህወሓት በኢህአዴግ ምርጫ ህወሓት ተሸንፎል፣ በብልፅግና ፓርቲም ምሥረታ ራሱን አግልሎል፡፡  በኖቨምበር  24 ቀን  2020 እኤአ በህግ ሊታገድ የሚያስችሉ የሃገር ክህደት ወንጀሎች በመፈጸም በህግ ተሠርዞል፡፡ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት በስብዓዊ ጋሻነት አፈናና ጭቆና ከተያዘበት የባርነት ሠንሠለት ከአርባ ስድስት አመታት በኃላ ነፃ ወጥቷል፡፡

  • የወያኔ ጁንታ በሃገር ክህደት በመንግሥት ግልበጣ ወንጀል ተጠያቂ ነው፡፡ ኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት የክልል ሥልጣንና ተግባር ‹‹የክልሉን የፖሊስ ኃይል ያደራጃል ፣ይመራል፣የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ያስጠብቃል፡›› ይላል አንቀጽ 52፡፡ በህገ-መንግሥቱ  መሠረት ክልሎች የፖሊስ ሠራዊት ኃይል ብቻ ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡ የትግራይ ክልል 250000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ) ልዩ ሓይል፣ የአማራ ክልል 300000 (ሦስት መቶ ሽህ) ልዩ ኃይል፣ የኦሮሚያ ክልል 400000 (አራት መቶ ሽህ) ልዩ ኃይል፣ የሱማሌ ክልል 40000 (አርባ ሽህ) ፣ የጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሃረሪ፣ አፋር፣ ደቡብ (ሲዳማ ክልል አንድ ሽህ ልዩ ኃይል)፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት 250000(ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ) ይገመታል፡፡ ሁሉም ክልሎች የራሳቸው ሚሊሽያና ፖሊስ ኃይል በተጨማሪ አላቸው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ስህተት ለመማር የየክልሉን የፖሊስ ኃይል ማደራጀት መምራት ፣የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ማስጠበቅ ኃላፊነት ብቻ ሊኖራቸው ይገባል እንላለን፡፡

የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ( ትህነግ) ህገመንግሥቱ በመጣስ ክልሎች  ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀቶች  እንዲኖራቸው አደረገ፣ ቀስ በቀስ እየተጠናከሩ በመሄድ በክልሎች መኃል ተጨማሪ ኃይል የማሰባሰብ ክልሎች እርስበእርሳቸው የጎሪጥ እንዲተያዩ አደረጋቸው፡፡ በትግራይ ክልል የሚገኘውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በዘርና በብሔር አደረጃጀት ከፋፈለው የትግራይ ተወላጆች ሌሎችን በተለይም የአማራዎችን በመግደል፣ በማገትና መሳሪያ ዘርፈዋል፡፡ ወያኔ የሠራዊቱን  ሃገራዊ ፍቅሩንና ብሄራዊ ክብሩን በማዋረድ ሠራዊቱን በዘርና ኃይማኖት ፍጅት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን በመቀስቀስና የዘር ጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት  ሃገሪቱን እንደ ሶሪያ፣ የመን፣ ሊቢያ ሊያፈርሳት ሞክሮ ነበር፡፡ ወያኔ የፖለቲካ ሴራ ዳግም የማዕከላዊ መንግሥት ስልጣን ለመጨበጥ የሰሜን እዝ ላይ ወንጀል ቢፈፅምም እንኮን ሃገር ለማፍረስ  ሠራዊቱን  ተባባሪ ማድረግ አልተቻለውም፡፡ ትግራይ ክልል የሚኖር የኢትዮጵያ ሠራዊት የወያኔ ተባባሪ ሳይሆን፣ የወያኔ መሪዎችን አስሮ ለፌዴራል መንግስት እንደሚያስረክባቸው ምንም ጥርጥር የለንም፡፡ የወያኔ ጁንታ በሃገር ክህደት በመንግሥት ግልበጣ ወንጀል ተጠያቂ ነው፡፡ ወያኔ በህዝብ የተጠላው በአንድ ዘር ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ፖሊስ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሽያ እያለ በክልሎች የዘር ፖለቲካ በመትከልና በከፋፍለህ ግዛው ብሂል በመጠቀም ለሃያ ሰባት አመታት ገዝቶ ወደቀ፡፡ ወታደራዊ ሳይንስ ዓለም አቀፋዊ ሙያ ሆኖ ለአንድ አገር ይቆማል እንጂ ለይቶ ለአንድ ዘር የመቆም ቃል ኪዳን ገብቶ አያውቅም ለዚህ ነው  ‹‹ወታደር ሀገር እንጂ ብሔር የለውም!!!››የሚባለው ለዚህ ነው፡፡

ትግራይ የጦር አበጋዞች መንግስት የሌሎች ክልሎች የጦር አበጋዞች መንግስት ምን ይማራሉ?

የአማራ፣ የኦሮሞ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ሃረሪ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ደቡብ፣ ሲዳማ፣ የጦር አበጋዞች መንግስት ከትግራይ ክልል የጦር አበጋዞች መንግስት ምን ይማራሉ የፌዴራል መንግሥት ምን ሊማር ይገባዋል?

ከክልል ፖሊስ በስተቀር ያሉ የክልል ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀትች ሙሉ በሙሉ ከክልሎች እጅ አውጥቶ በፌደራል መዋቅር ስር ማድረግ ያስፈልጋል እንላለን፡፡ ‹‹የጎሳ ፖለቲካ ጡዘት ሰማይ በነካበት እንደ ኢትዮጵያ አይነት አገር ውስጥ በብሔር የተዋቀረ የክልል ታጣቂ ልዩ ኃይል ወይም ሚሊሻ ማደራጀት ማለት የተጠመደ ፈንጅ በጀርባ አዝሎ እንደመዞር ነው። ክልሎች በአገር ውስጥ ያሉ አገሮች ሆነው ተዋቅረዋል። በዛ ላይ አወቃቀራቸው ቋንቋና ብሔርን መሰረት ያደረገ ነው። የብሔር ፖለቲካው እያመሳት ላለች አገር በብሔር የተደራጁ ታጣቂ ኃይሎች እያሰለጠኑ እና እያስታጠቁ በየክልሉ ማስቀመጥ ካየነው በላይ ብዙ ግፍ እንድናይ እና ኢትዮጵያንም በቀላሉ ወደ ዘር ተኮር ግጭት ከመውሰድም በላይ የአክራሪ ቦድኖች መፍለቂያነት እና ወደ ሽብር ቀጠና ሊለውጣት ይችላል። ከወዲሁም አንዳንድ ምልክቶች በግላጭ እየታዩ ነው፤በክልሎች መካከል ያለው ውጥረት እና ትከሻ መለካካት በየጊዜው ግጭቶችን አስከትሏል። አሁንም ተፋጠው፣ ጉድጓድ ምሰው እና ቃታ ስበው ለፍልሚያ ቀን የሚጠብቁ አሉ። ለዚህም የትግራይና የአማራ ክልል ፍጥጫ ጥሩ ማሳያ ነው።›› በብሔር የተዋቀረውን የጸጥታ አስከባሪ ኃይል ሙሉ በሙሉ በመበታትን ወደ ሁሉም የአገሪቷ ክፍል ማሰባጠር እና በእያንዳንዱ ክልል ውስጥ ያለው ታጣቂ ኃይል ከሁሉም ብሔር የተወጣጣ እንዲሆን ማድረግ፣ በየክልሉ ያለውን ስብጥር ኃይልን በበላይነት የሚመሩትንም አዛዦች እንዲሁ በተሰባጠረ መልኩ ማዋቀር፣ ይህን ኃይል በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት አይምሯቸው ውስጥ ያለውን የብሔረተኝነት ስሜት በሂደት እንዲቀይሩና ያለመድሎ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ደህንነት ዘብ እንዲቆሙ ማድረግ ይገባል እንላለን።

  • በኢትዮጵያ ጠቅላይ ጦር ሠፈር የመሣሪያ ክምችን በሁሉም እዞች ተመጣጣኝ ማድረግ፤- የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ጦር ሠራዊት፣አየር ወለድ፣ ዓየር ኃይል፣የፖሊስ ሠራዊት ወዘተ፤ ከላይ ከዋናው ኤታ ማጆር ሹም ጀምሮ ዕዞች፣ ክፍለ ጦሮች፣ ብርጌዶች፣ ሬጅመንቶች፣ ሻለቃ፣ ሻምበል እስከ ጋንታና እስከ ታች ጓድ ድረስ የሠራዊቱ ዋና ጦር ሠፈር በትግራይ የወያኔ የዘር ሃረግ ስልጣኑ የተያዘና በትግራይ  ክልል ውሰጥ የጦር መሳሪያው  መከማቸቱ ሆን ተብሎ በወያኔ የተነደፈ የአናሳ ዘውጌኛነት የስነ-ልቦና ደዌ/በሽታ ነው፡፡ ወያኔ ኢትዩጵያን ካልገዛና ካልመራ ህዝቡ ይበቀለናል በሚል እብሪትና ፍርሃት የተነሳ፤ የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊትና የመሣሪያ ክምችት በሙሉ በትግራይ ክልል ውስጥ መገኘቱ በትረ-ሥልጣናቸውን በቀጣይና በዘለቄታ ከደደቢት ዋና ጠቅላይ ጦር ሠፈር ለመቆጣጠር የታቀደ ዋና ብልሃት ነው፡፡ ከዚህም በመማር የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት የመሣሪያ ክምችን በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምስራቅና ምዕራብ መከላከያ እዞች  ተመጣጣኝ ክምችት እንዲኖር ማድረግ ከሰሜን እዝ የምንማረው ትምህርት ስለሆነ በግዜው ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል እንላለን፡፡
  • የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት የሰው ኃይል ልማት ድልድል ተመጣጣኝ ማድረግ፡-፣የህወሃት መከላከያ ሠራዊት፣ጦር አበራዞች  ከላይ ከዋናው ኤታማጆር ሸሙ ጀምሮ ዕዞች፣ ክፍለ ጦሮች፣ ብርጌዶች፣ ሬጅመንቶች፣ ሻለቃና፣ ሻምበል  ድረስ የሠራዊቱ ዋና ጦር ሠፈር በትግራይ የወያኔ የዘር ሃረግ ስልጣኑ የተያዘና በትግራይ  ክልል ውሰጥ የጦር መሳሪያው  መከማቸቱ ሆን ተብሎ በወያኔ የተነደፈ የአናሳ ዘውጌኛነት የስነ-ልቦና ደዌ/በሽታ ነው፡፡ ወያኔ ኢትዩጵያን ካልገዛና ካልመራ ህዝቡ ይበቀለናል በሚል እብሪትና ፍርሃት የተነሳ፤ የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊትና የመሣሪያ ክምችት በሙሉ በትግራይ ክልል ውስጥ መገኘቱ በትረ-ሥልጣናቸውን በቀጣይና በዘለቄታ ከደደቢት ዋና ጠቅላይ ጦር ሠፈር ለመቆጣጠር የታለመ ነበር ከዚህ ስህተታቸው በመማር የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት የሰው ኃይል ልማት ድልድል ተመጣጣኝ ማድረግ፡
  • ወታደራዊ ትርኢት (Military Parade)፡-የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ወታደራዊ ትርኢት በተከታታይ በትግራይ ክልል ውስጥ ለአመታት መታየት በቀሪው የኢትዩጵያ ህዝብ ላይ ያሳደረው ጫና በሠራዊቱ ላይ የኔነት ስሜት (Sense of Belongingness) አሳጥቶታል፡፡ የወያኔ ሠራዊት እንደ ጥንቱ ከህዝብ ጋር አብሮ ቆርሶ ፣አብሮ ጎርሶ፤ አብሮ አርሶ ፣አብሮ ዘርቶ ይባልለት የነበረ ወርቃማ ዘመንን በዘረኝነት አጨለመው፣ ቀሪውን ዜጋ ሁሉ የሁለተኛ ዜግነትና ብሄር ብሄረሰብ መታወቂያ እየሰጠ ይገዛ ጀመር፡፡ የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት፤በወያኔ የጦር አበጋዞች ማለትም የጦር መኮንኖች እዝና ቁጥጥር (Command and Control)  ተወጥሮና ተጠርንፎ ሲሰቃይ ሃያ ሰባት አመታት ተቆጥሮል፡፡ የህወሃት የጦር አበጋዞች መንግስት የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፀበል እየረጨ፣ የልማታዊ መንግስት ቄጤማ እየነሰነሰ፣ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ሸማ በየአምስቱ አመት እየቆረጠ ከሰማይ ደመና፣ ከምድር ዉሃ አጠፋ፡፡ የህወሃት የጦር አበጋዞች መንግስት በህገ-መንግስት ስም፣ በዴሞክራሲ ስም፣ በግለስብና በህዝብ ላይ ፍጹማዊ አገዛዝ (Totalitarian) በመዘርጋት ለሃያ ሰባት አመታት በግፍ ገዝተዋል፡፡ የወያኔን ግፍ ያዩ የትግራይ ወጣቶች ከሌሎች ኢትዩጵያዊ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጎን ቆመዉ  የህወሃት የጦር አበጋዞች መንግስት ጠቅላይ ጦር ሠፈር ለማጋየት ታጥቀው መነሳት ብቸኛ አማራጭ ነው፡፡
  • ጁንታ የባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ተቆማትን ነቀላና ተከላ፡-የህወሓት ጁንታ አጋር የነበረው የባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ተቆማትን በዘርና ኃይማኖት የተደራጁ ነቀላና ተከላ ማድረግ አንገብጋቢ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መተግበር ለቀጣዩ የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ልማት በር ከፋች ይሆናል፡፡ በዘርና ኃይማኖት ላይ የተደራጁትን የባንክና ፋይናንስ ስርዓት አስወግዶ ዘመናዊ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የዘመነ የዲጂታል ዘመን የባንክ ሥርዓት በመገንባት ወደ አዲስ ዘመን መሸጋገር ግድ ይላል፡፡ በሃገሪቱ ባንኮች አሰራር ስር የሰደደውን ሙስና፣ የዘረኝነት ዝምድና አሰራር፣ ድብቅ አስራር፣ ተጠያቂ አለመሆን ወዘተ ሊወገድ ይገባል እንላለን፡፡ የህወሓት ጁንታ አጋር የነበረው የባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ተቆማትና ማይክሮ ፋይናንስ ብልሹ አሰራር የብድር አሰጣጥ፣ አሰባሰብ ዘረኛና አድሎዊ አስራር ፣ ተጋልጠው በመውጣት ትምህርት ሊቀሰምባቸው ይገባል እንላለን፡፡

የሕገ- መንግሥት  አንዴም ይሻራል አንዴም ይፀድቃል!!!

በኢትዮጵያ ሃገረ መንግሥት ግንባታ ታሪክ አራት ሕገ-መንግስቶች ጸድቀው ተሸረዋል፡፡ የ1931 እኤአ የቀኃሥ ዘመን ህገመንግስት፣ የ1955 እኤአ የኢትዮጵያ ሕገመንግስትን ወታደራዊው ደርግ አሻሽሎ አጸደቀ፣ በ1987 እኤአ  ወታደራዊው ደርግ አዲስ ህገመንግስት አፀደቀ፣ በ1995 እኤአ ህወሓት /ኢህአዴግ አዲስ ህግመንግስት ለአለፉት ሃያ አምስት አመታት አገልግሎል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ  ህገመንግስቱን ማፅደቅ፣ ማሻሻልና መሻር ሙሉ መብት አለው፡፡

Ethiopia has had four constitutions:1931 Constitution of Ethiopia,1955 Constitution of Ethiopia,1987 Constitution of Ethiopia and 1995 Constitution of Ethiopia. A proposed revision of the 1955 constitution was released in 1974, but it had no legal effect, and was soon forgotten in the events of the Ethiopian Revolution. (Constitutions of Ethiopia – Wikipedia) From Wikipedia, the free encyclopedia

ህገ-መንግስት፤- ከህወሓት ኢህአዴግ የፖለቲካ ሴራን ለመበጣጠስ የወያኔን ህገ-መንግስት በአዲስ ተክቶ ይሄን የአባላሽኝ ዘመን አልፈን አዲሲቶን ኢትዮጵያ በእውነትና በሃቅ መምራት ይጠበቅብናል፡፡ የህወሓት ኢህአዴግ ጅኦ ፖለቲካል ካርታ ሃገሪቱን ክልል ግዛትና ድንበር በዘር የሸነሸነ በመሆኑ የሃገሪቱ ዜጎች በድንበር ግጭት ወደማያባራ ጦርነት መግባታቸው ወያኔ ሕገመንግስትን የተቀበረ ቦንብ ነው፡፡

ጅኦ ፖለቲካል ካርታ ይወገድ፡- በኢትዮጵያ ዜጎች በመላ ሃገሪቱ ተዘዋውረው እንዲሰሩ ከተፈለገና በፈለጉበት ቦታ መኖር እንዲችሉ ከተፈለገ ይህ በዘር ላይ የተሸነሸነ ሰው ሰራሽ  ጅኦ ፖለቲካል ካርታ መወገድ አለበት፡፡

በኢትዮጵያ የክልል መንግሥት ድንበሮች/ ወሰኞች፣ (Regional state borders) የኦሮሚያ ክልል 9 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የአማራ ከልል 5 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የትግራይ ክልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የአፋር ከልል 6 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የሱማሌ ከልል 5 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የደቡብ ከልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የጋምቤላ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የሃረሪ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉዋቸው፡፡  በኢትጵያ የክልል ብሄራዊ መንግሥታት  የመስፋፋት ፖሊሰ፣ ሃገሪቱን ወደ ማያባራ የድንበርና የወሰን ግጭት እንደሚዳርጋት ነብይ መሆን አይጠይቅም፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም ከቌንቌ ይልቅ በጂኦግራፊያዊ አቀማማጥና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ላይ በማተኮር ስነምድራቸው ተስማሚና አንድ ዓይነት የሆኑትን አግሮ ኢንድስትሪያል ልማት፣ (የስኳር ልማት፣ የሠሊጥ ልማት፣ የቡና ልማት) በማስፋፋት እንዲሁም የአግሮ ኢንዱስትሪና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ተመጋጋቢ ሆነው በማደግ ለህዝብ የሥራ እድል በመፍጠርና ከውጭ የሚመጡ ምርቶችን በመተካት የዘይት፣ የስኳር፣ የቢራ መጥመቂያ ገብስ፣ ስንዴ ምርት፣ ወዘተ ስነምድራዊ አቀማመጥ ላይ ያተኮረ ቢሆን በሃገር ውስጥ ማምረት ይቻላል፡፡

የጦርነት አዋጅ፡- ወያኔ የተሸነፈው ጦርነት ገጥሞ ነው!!! ዘመኑ በዴሞክራሲያዊ መንገድ በሃሳብ ልዕልና ብቻ የማሸነፍ ጥበብን መካን ነው፡፡ ወያኔ ጁንታ ሁሌ በኃይል እርምጃ፣ በሽብርተኛነትና በማፍያ ስውር ስራ የተካነ  ድርጅት በመሆኑ  ለእራሱም ለህዝብም አልበጀ!!! የቀበረው ፈንጂ እራሱኑ አጠፋው፡፡

ዴሞክራሲያዊ መንገድ ችግሮቻችንን በሰለጠነ መንገድ በዴሞክራሲያዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ብቻ ለመፍታት መሞከር ዘመናዊነት ነው፡፡ ህወሓት የኃይል አማራጭ በመጠቀም ምንም የማያውቁ ወጣቶችን ለጦርነት በመማገድ ህይወታቸውን አጥተዋል ፣ ቆስለወል፣ ተሰደዋል፡፡ መሰረተ ልማቶች ወድመዋል፣ሃገሪቱ በውጭ ምንዛሪ የገዛቻቸው የጦር መሣሪያዎች በነበሩበት የጦር ካንፖች ጋይተዋል፣ ታንኮቻችን ወድመዋል፣ የጦር ማጋጋዣ መኪኖች ተቃጥለዋል፣ በውይይት እንጂ  በኃይል የሚፈታ ምንም ነገር የለም፡፡

የማንነትና የድንበር ጥያቄ፡-በህወኃት ዘመን የተቀበረ ፈንጂ በተለይ የማንነትና የድንበር ጥያቄ አፈታት ዙሪያ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ራያ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሃዋሳ፣ አዳማ ወዘተ በመላ ሃገሪቱ በተለያየ ጊዜ የተነሱ የማንነትና የድንበር ጥያቄ በብልሃት መፈታት የሁሉም ምሁራንና ህዝብ ግዴታ ነው እንላለን፡፡ ከህገመንግሥቱ የዘር ፌዴራሊዝምን ሥርዓትና አወቃቀር የክልላዊ መንግሥት አደረጃጀት ወሰንና ድንበርን በማስቀረት ግጭቶችንና ጦርነትቶችን ማስቀረት ይቻላል፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሃገሪቱ ውስጥ ተዘዋውሮ መስራት፣ ሃብትና ንብረት ማፍራት፣ መምረጥና መመረጥ መብት እንዲኖረው ማድረግ ይቻላል፡፡ የብሄር ብሄረሰቦች ራሳቸውን የማስተዳደር መብት፣ በቌንቌቸው መጠቀም፣ ባህላቸውንና ቅርሳቸውን መንከባከብ፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት በእኩልነት፣ በወንድማማችነትና በነጻነት አብሮ በህብረት የመኖር መብታቸውን የሚያስከብርላቸው ህገመንግሥት ማፅደቅ ያደጉ ሃገራቶች ታሪካዊ የስልጣኔ ዴሞክራሲያዊ ግንባታ ሂደት መሆኑን ማስተዋል ያሻል እንላለን፡፡

የወያኔ ጁንታ የፌዴራሊስቶች ህብረት መሪ፡-በኢትዮጵያ ክልሎች ያንጃበበውን አደጋና ጦርነት ከወዲሁ አጢነው ለዚህ ለውጥ መሳካት ካልተባበሩ በዘር ያደራጁት የታጠቀ ኃይል ተንሸራቶ አክራሪዎች የወያኔ ጁንታ እጅ የወድቆ  የጥቃት ኢላማዎች የሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊትን በማድረግ የፈጸሙት የሃገር ክህደትና ሽብርተኛነት በወያኔ ጁንታ ላይ የተባበረ ክንድ ተመክቶል፣ ወያኔም ድባቅ ተመቶል፡፡ በዘር ተደራጅቶ በዘር የታጠቀ የዘር ፍጅትን ያፋጥናል የምንለው ለዚህ ነው። የወያኔ ጁንታ እራሱን የፌዴራሊስቶች ህብረት መሪ በማድረግ ያሰባሰባቸው ኃይሎች ህወኃት፣ ኦነግ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ፣ ሲአን፣ ኦብነግ የመሳሰሉት ይህን ዘረኛ ህገመንግሥት በመደገፍ አይቀየርም አይሻሻልም አይነኬ ነው ! ሲሉ ከርመዋል፡፡ የወያኔ ጁንታ የፌዴራሊስቶች ህብረት መሪ ‹‹በሀገራችን ውስጥ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ግምባር ቀደም ተጠቂ ይሁኑ እንጂ፣ “መጤ”ና “ኗሪ” በሚል የጥላቻ ትርክት የተቀመረው ሕገ-መንግሥት ሌሎች ብሄረሰቦችንም ለጥቃት አጋልጧቸዋል። ጉራጌዎች፣ ስልጤዎች ጋሞዎች…ወዘተ ተጠቂዎች ሆነዋል። በሃይማኖትም ክርስቲያን ኦሮሞዎች የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል ይገኛሉ። የፌዴሬሽኑን ሕገ-መንግሥትና የክልል ሕገ-መንግሥቶችም፣ ተቀርፀው የተዋቀሩት አንዱን ‹ኖሪ/ባለቤት› የአንደኛ ደረጃ ዜጋ ሌላውን ‹መጤ/ ሠፋሪ›  በሚል የሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ማዕከልነት ላይ የተመሠረቱ ናቸው።  በቡራዩ፣ በአርሲ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በሻሸመኜ፣ በዝዋይና በባሌ እስከ ሦስት ጊዜ ድረስ የተካሄደው ጥቃት፣ ባመዛኙ የአማራና ሌሎችንም “መጤ” ተብለው የተሰየሙ ብሄረሰብ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ፣ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞችንና የዕምነት ቤቶችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ነው። የብልፅግና ፓርቲ መሪ ዶክተር አብይ አህመድ ይሄን ምክር ተጠቅመው የኢትዮጵያን እናቶች፣ ህጻናትና፣ ሁሉን ዜጎች ከዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጀኖሳይድ) ከቡራዩ እስከ ሻሸመኔ፣ ከወለጋ እስከ ሃረር፣ ከጉራፈርዳ እስከ ማይካድራ ሊታደጉትና ህይወታቸው ሊጠበቅ ይገባል፡፡

የፖለቲካ ኃይል አሰላለፍ፡- በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይል አሰላለፍ  ህወሓት ወደመቃብር ወርዶል፡፡ ብልጽግና ፓርቲ የህወሓት የላይ አመራር ብቻ በማስወገድ የበታች አከላቱን አጠናክሮ ህወሓትን ከመቃብር ማስነሳት እንደሚሹ ዶክተር አብይ አህመድ በንግግራቸው ገልጸዋል፡፡ የህወሓት ሜታሞርፎስስ ውልደት፣ እድገት፣ እርጅናና ሞት  ዕደቱን ወደ ኃላ መመለስ ግን ዶክተር ዐብይ አይቻላቸውም፡፡ ህወሓት እንደ መለስ ዜናዊ ተቀብሮል፣ ይሄን ሃቅ ያልተረዳ የህወሓትን ህገመንግሥት፣ የዘር ፌዴራሊዝም፣ የክልልመንግሥት የክልል ወሰንና ድንበር ወዘተ ዳግም ለመተግበር የሚመኝ ከወያኔ ያልተማረ ተረኛና ዘረኛ አመለካከት ያልተላቀቀ ነው እንላለን፡፡ በፓርላማ ወያኔ በሽብርተኛነት እንዲፈረጅ ብዙ የፓርላማ አባላት ሲጠይቁ ዶክተር ዐብይ ሆን ብለው መልስ ሳይሰጡ  አልፈውታል፡፡ ዶክተር አብይ ከ2013ዓ/ም ስድስተኛ ምርጫ አሸናፊ ፓርቲ የሚመሠረተው መንግሥት ህገመንግስቱን ማሻሻል፣ መቀየር ፣ ማፅደቅ ሥልጣን እንዲኖረው ሃሳብ አቅርበዋል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የማንነትና የወሰን ጥያቄ ጠያቂዎች፣ ወዘተ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛ ዙር ምርጫ በደንብ በመሳተፍና በመመረጥ ህገመንግሥቱን ለመቀየር፣ ወይም  ለማሻሻል  ከአሁኑ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በምንም መንገድ ወደ ግጭትና ጦርነት ከመግባት መቆጠብ አስፈላጊ ነው እንላለን ከጦርነት ይልቅ በሠላማዊ ዴሞክራሲያዊ መንገድ ብቻ መጠቀም ያሻል፡፡

የብዙሃን ድርጅቶች መጠናከር፡ በወያኔ ጁንታ ላለፈው ሃያ ስባት አመታት የታፈኑ የመምህራን ማህበር፣ የሠራተኛ ማህበር፣ የተማሪዎች ማህበራት፣ የታክሲ ሹፌሮች ማህበር፣ የሴቶች ማህበር ወዘተ ተጠናረው በመውጣት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ ያስፈልጋል እንላለን፡፡

የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት፡-የህሊና እስረኞች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣  ልደቱ አያሌው፣ አስቴር ስዩም፣ይፈቱ!!!  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

Leave a Reply